በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ለኢትዮጵያ 97 ሚሊየን ዶላር ሰጠች

ጌል ስሚዝ፤ የዩኤስኤአይዲ አስተዳዳሪ (ፋይል ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ/AP)
ጌል ስሚዝ፤ የዩኤስኤአይዲ አስተዳዳሪ (ፋይል ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ/AP)

ኢትዮጵያ ለገጠማት የምግብ እጥረት ማሟያ የሚውል የዘጠና ሰባት ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ እርዳታ እንደምትሰጥ ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች።

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት

ኢትዮጵያ ለገጠማት የምግብ እጥረት ማሟያ የሚውል የዘጠና ሰባት ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ እርዳታ እንደምትሰጥ ዩናይትድ ስቴትስ አስታወቀች።

የሃገራቸውን አዲስ እርዳታ ያስታወቁት የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲዋ አስተዳዳሪ ጌል ስሚዝ ናዠው።

ጌል ስሚዝ የዩናይትድ ስቴትስን የልዑካን ቡድን መርተው ዛሬ - ዕሁድ፤ ጥር 22/2008 ዓ.ም በተጠናቀቀው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ተገኝተዋል።

የዩኤስኤአይዲዋ ኃላፊ አዲስ አበባ ላይ የተሰበሰቡ ሲሆን በስብሰባው ላይ ተጨማሪውን እርዳታ ካስታወቁ በኋላ ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ 97 ሚሊየን ዶላር ሰጠች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:46 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG