በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማልያ ኰማንዶዎች በዮናትድ ስቴትስ ኃይሎች በመታገዝ በታች ሸበሌ ክልል የሄሊኮፕተር ወረራ አካሄዱ

የሶማልያ ወታደር አል-ሸባብ በሞቃዲሾ በሚገኘው የፖሊስ ትራፊክ ቢሮ ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ጥበቃ ላይ እ.አ.አ. 2016 /ፋይል ፎቶ/
የሶማልያ ወታደር አል-ሸባብ በሞቃዲሾ በሚገኘው የፖሊስ ትራፊክ ቢሮ ላይ ጥቃት ካደረሰ በኋላ ጥበቃ ላይ እ.አ.አ. 2016 /ፋይል ፎቶ/

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን የኦፐሬሽኑን መካሄድ አረጋግጠው፣ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችን ሚና ግን በግልጽ አልተናገሩም።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ የሰለጠኑ የሶማልያ ኰማንዶዎች በዮናትድ ስቴትስ ኃይሎች በመታገዝ በታች ሸበሌ ክልል ቶራቶሮ መንደር ውስጥ ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት የሄሊኮፕተር ወረራ ማካሄዳቸውን፣ የሶማልያ ባለሥልጣናትና የአይን ምስካሪዎች አስታወቁ።

የቶራቶሮው መንደር ነዋሪዎች እንዳስታወቁት፣ በሄሊኮፕቴር የታገዙት ወታደሮች መንደሩ ላይ ጥቃት ካካሄዱ በኋላ ተመልሰው ወደ ካምፓቸው አምርተዋል።

የኬንያ ወታደሮች ሄሊኮፕተር በኬንያ-ሶማልያ ድንበር እ.አ.አ. 2012 /ፋይል ፎቶ/
የኬንያ ወታደሮች ሄሊኮፕተር በኬንያ-ሶማልያ ድንበር እ.አ.አ. 2012 /ፋይል ፎቶ/

የሶማልያ የደኅንነት ባለሥልጣን መሃመድ ኑር ጋቦ በተናገሩት ቃል፣ የሶማልያ ወታደሮች ያነጣጠሩት በአንድ የአል-ሸባብ ጦር ሰፈር ላይ መሆኑን አመልክተው፣ ዓላማቸውንም በተሳካ ሁኔታ ከግብ አድርሰዋል ብለዋል።

አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን የኦፐሬሽኑን መካሄድ አረጋግጠው፣ የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችን ሚና ግን በግልጽ አልተናገሩም።

ወታደሮች ዛሬ ማለዳ ላይ በሰጡት ማስጠንቀቂያ ነዋሪዎች ከቤታቸው እንዳይወጡ፣ ስልኮቻቸውንም እንዲዘጉ አሳስበዋል። ሃሩን ማህሩፍ ያጠናቀረውን ዘገባ፣ አዲሱ አበበ አቅርቦታል።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG