ዋሽንግተን ዲሲ —
አንድ ከፍተኛ የስለላ ባለሥልጣን ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ እንደገለጹት፣ እራሱን እስላማዊ መንግሥት ብሎ የሚለውን ቡድን የሚደግፉ የሶማልያ አማጽያን ቁጥራቸው እየተበራከተ ከመሄዱም በላይ፣ እንደ የመን ከመሳሰሉ አገሮችም እርዳታ እያገኙ ናቸው ብለዋል።
ከ20-30 በሚሆኑ ሰዎች የተመሰረተው ቡድን ዛሬ ከ100-150 ተዋጊዎችን ማሰለፉን ነው ባለሥልጣኑ የተናገሩት።
የአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ሶማልኛ አገልግሎት ባልደረባችን ሃሩን ማሩፍ ያጠናቀረውን ዘገባ አዲሱ አበበ አቅርቦታል፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።