በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሊያ በአሜሪካ ኤምባሲ ከፈተች


ሶማሊያ በአሜሪካ ኤምባሲ ከፈተች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:35 0:00

ሶማሊያ በአሜሪካ ኤምባሲ ከፈተች

ሶማሊያ ዋሺንግተን ዲ.ሲ ውስጥ ኤምባሲ የከፈተችውከሃያ አራት ዓመታት በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

በአሜሪካ የሶማሊያ ኤምባሲ በተዘጋ በሩብ ምዕት ዓመቱሲከፈት በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የሶማሊያየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲሰላም ኦማር “ከመገለልጨለማ መውጣታችንን ያበሰረ ታላቅ ዕለት ነው” ሲሉበሁኔታው የተሰማቸውን እርካታ ለቪኦኤ ገልፀዋል።

“… በሶማሊያ የቅርብ ታሪክ ውስጥ እጅግ ከፍተኛትርጉም ያለው ቀን ነው፤ ከጨለማው መውጣታችንን ያበስረናል፤ የዓለም አካል መሆናችንን ያሣያል፡፡ብዙ ጠቃሚ ውሣኔዎች በሚተላለፉባት፣ ብዙ ችግሮችበሚፈቱባት ዋሺንግተን ዲሲ እንገኛለን፡፡ በወዳጆቻችንመካከል ነን፡፡ በዩናይትድ ስቴትስ ወንድሞቻችን፣አጋሮቻችን መካከል እንገኛለን፤ ሶማሊያ ጨርሶአትጠፋም” ብለዋል ሚስተር አብዲሰላም ኦማር።

ከጨለማው መውጣታችንን ያበስረናል፤ የዓለም አካል መሆናችንን ያሣያል፡፡ብዙ ጠቃሚ ውሣኔዎች በሚተላለፉባት፣ ብዙ ችግሮችበሚፈቱባት ዋሺንግተን ዲሲ እንገኛለን።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብዲሰላም ኦማር

በሌላ በኩል ደግሞ ዩናይትድ ስቴትስ በበርካታ የትብብርአካባቢዎች ከሶማሊያ ጋር መሥራቷን እንደምትቀጥልየዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳትሚኒስትር ሊንዳ ቶማስ ግሪንፊልድ አረጋግጠዋል።

ፀጥታ፣ ልማት፣ አስተዳደር የቅድሚያ መስኮችመሆናቸውንና ሶማሊያ ምርጫ ለማካሄድ ወደፊትእንድትገፋ ሃገራቸው እገዛ እያደረገች መሆኗን ረዳትሚኒስትሯ ገልፀው የሶማሊያን መፃዒ ጊዜ የሚመለከቱትበብሩህ ተስፋ መሆኑን አምባሳደር ግሪንፊልድተናግረዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን ዘገባ ያዳምጡ።

ሶማሊያ በአሜሪካ ኤምባሲ ከፈተች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:46 0:00

XS
SM
MD
LG