በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እንካ ሰላንቲያ - የደቡብ አፍሪካና የአሜሪካ ዲፕሎማሲ


የገዢው ፓርቲ ቃል አቀባይ ዚዚ ኮድዋስ /ፋይል ፎቶ/
የገዢው ፓርቲ ቃል አቀባይ ዚዚ ኮድዋስ /ፋይል ፎቶ/

“ዩናይትድ ስቴትስ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ለማጣጣል ሙከራ ታደርጋለች” ሲሉ፣ የገዢው ፓርቲ ቃል አቀባይ ዚዚ ኮድዋስ ክስ አሰምተዋል። የመንግሥታቱ ቃል አቀባዮች አስተባብለዋል።

“ዩናይትድ ስቴትስ በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጠውን የደቡብ አፍሪቃ መንግሥት ለማጣጣል ሙከራ ታደርጋለች” ሲሉ፣ የገዢው ፓርቲ ቃል አቀባይ ዚዚ ኮድዋስ ክስ አሰምተዋል።

የሁለቱ መንግሥታት ተጠሪዎች ግን በሁለቱ መንግሥታት መካከል ያለው ግንኙነት የምንኮራበት፣ የሞቀ፣ የልብ ለልብና እንደቀድሞው ጠንካራ ነው ይላሉ።

የገዥው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ቃል-አቀባይ ወቀሣቸውን ያሰሙት “ሰንዴይ ታይምስ” የሚባለው የእንግሊዝ ጋዜጣ “የደቡብ አፍሪቃው ዘረኛ አገዛዝ እ.አ.አ. በ1962 ዓም ኔልሰን ማንዴላን ሲያስር የአሜሪካው ማዕከላዊ የስለላ ተቋም ማለትም - ሲአይኤ እገዛ ነበረበት” ብሎ በመዘገቡ ነው።

ጋዜጣው አሁን በሕይወት የሌሉ አንድ የሲአይኤ ወኪልን ሲጠቅስ «ማንዴላ የኮምዩኒዝም አቀንቃኝ ናቸው ብላ ዩናይትድ ስቴትስ ታምናለች» ያሉትን አስታውሶ ነበር የፃፈው።

ማንዴላ ዘረኛውን አገዛዝ በመቃወማቸው ለሃያ ሰባት ዓመታት እሥር ቤት ውስጥ እንዲማቅቁ ተደርጓል።

ባልደረባችን አኒታ ፓወል ያጠናቀረችውን ዘገባ፣ ሰሎሞን አባተ አቅርቦታል።

እንካ ሰላንቲያ - የደቡብ አፍሪካና የአሜሪካ ዲፕሎማሲ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:05 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG