ደቡብ አፍሪቃ ኤል ኒኖ ባስከተለባት ድርቅ ምክንያት ለተከታታይ የምግብ ዋስትና አደጋ ተጋልጣለች። ኤል ኒኖ የተባለው የአየር ለውጥ በየጥቂት አመታት በፓሲፊክ ኢኳቶርያል ክፍል ባለው የውቅያኖስ ጠለል ላይ ውሃው እንዲሞቅ በማድረቅ ድርቅ ያስከትላል።
የደቡብ አፍሪቃ የውሀ ሀይል ዝቅ እያለ ሄዷል። ዋናው የሀገሪቱ ምግብ የሆነው ቦቆሎ ክምችትም እያሽቆለቆለ በመሄዱ ለአራት ወራት ያህል ብቻ የሚያዘልቃት ነው የተረፈው።
“እስከ መጪው ግንቦት ወር ባለው ጊዜ ውስጥ ነጭና ብጫ በቆሎ ሊያጥረን ይችላል። ስለሆነም እስከዛ ባለው ጊዜ ውስጥ በቂ ቦቆሎ እንዲኖረን ማድረግ ይኖርብናል።”
ጠብበብት እንደሚሉት በሰውና በእንስሳት ላይ አስከፊ ረሀብ እንዳይደርስ ለመከላከል ከአንድ ቢልዮን ዶላር በላይ የሚሆን ገንዘብ ያስፈልጋል።
በደቡባዊ አፍሪቃ በ 14 ሚልዮን የሚገመቱ ሰዎች ረሀብ እንደሚጠብቃቸው የአለም የጤና ድርጅት ዛሬ አስታውቋል። የተቸገሩትን ለመርዳት ከለጋሾች የሚገኘው ገንዘብ እያጠረ በመሄዱ ችግሩ በከባድ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።
ቦትስዋና በአምስት አመታት ውስጥ ያልታየ አይነት ከባድ ድርቅ እንደገጠማት አስታውቃለች። የውሀና የምግብ አቅርቦት እጥረት እየገጠማት እንደሆነም ጨምራ ገልጻለች።
ዚምባብዌም እንደዚሁ በድርቅ ምክንያት አብዛኛው ምርቷ ተኮላሽቶባታል። በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ቁም እንስሳት በድርቅ አልቀዋል። መንግስት በገንዘብ እጦት ምክንያት የመንግስት ሰራተኞችን ደመ-ወዝ በጊዜ ለመክፈል እያቃተው በመሆኑ እነሱም የእንሳቱ እድል እንዳይገጥማቸው ስጋት አለ።
በሚዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ምግብ ማግኘት ሊከድበቸው ይችላል የሚል ስጋት አለ። ከጆሀንስበርግ የተላከ የቱሶ ኩማሎ (Thuso Khumalo) ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል። አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች ከዚህ በታች ካለው ፋይል ያዳምጡ።