በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

መጤ-ጠል በደቡብ አፍሪቃዋ ደርበን


ደቡብ አፍሪቃ፣ ደርበን ውስጥ፣ በባዕዳን ላይ በተመሠሰረተ ጥላቻ (xenphobia) ስድስት ኢትዮጵያውያን ላይ አሰቃቂ ግድያ ተፈጽሞባቸዋል። ከሚፈጸመው ዝርፊያና ድብደባ ሌላ፣ ቤንዚን ተርከፍክፎባቸው ከነ ሕይወታቸው የተቃጠሉም አሉ። ፕሪቶሪያ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምበሲ ወደ ደርባን የሄዱ ባለሥልጣናት መኖራቸውም ተገልጧል።

በንግድ ሥራ የሚተዳደረው የደርባን ነዋሪ አቶ ዮናስ ፍቅሩ ባለፈው ዐርብ ቤንዚን ተርከፍክፎበት የሞተውን የ፳፬ ዓመቱ ኢትዮጵያዊ በየነ ሌሬቦ አስከሬኑ ትናንት ሰኞ እንደሚላክ ነበር የገለጸልን።

በዛሬው ፕሮግራማችን፣ ከደርባን የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ጽ/ቤት መሪዎች፣ ከአቶ ኤፍሬም ተስፋዬና አቶ ደስታ ላምቦሮ ጋር ተነጋግረን ሁኔታው ምን ላይ እንደደረሰ ተወያይተናል።

አቶ ደስታ ላምቦሮ፣ በደርባን የኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ጽ/ቤት አንዱ ኃላፊ ናቸው። ከኢትዮጵያውያኑ መገደል በኋላ ሌላ አዲስ ነገር አለ ወይ ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ አቶ ደስታ የአንድ ኢትዮጲያዊ ሱቅ መቃጠሉን ገልጸዋል።

በፖሊስ በኩል እየተደረገ ያለ ክትትል እንደሁ፣ ወይም ገዳዮቹ ስለመገኘታቸው የሚያውቁት ምንም መረጃ እንደሌላቸውም ገልጸዋል። ብቻ ግን፣ ፕሪቶሪያ ካለው ኤምበሲ፣ አምባሳደሩን ጨምሮ ባለሥልጣናት ወደ ደርባን በመግባት ላይ መሆናቸውን ሰምተናል ከማለት ያለፈ፣ እንዳላገኟቸው ነው ሁለቱም የኢትዮጵያ ማኀበረሰብ ጽ/ቤት ኃፊዎች የገለጹልን። አመጣጣቸውም የኢትዮጵያውያኑን መገደል አስመልክተው ከደቡብ አፍሪቃ በተለይም ከደርባን ባለሥልጣንት ጋር ለመነጋገር መሆኑን እንደሰሙ ተናግረዋል።

አምባሳደሩን ለማግኘት ስልክ ደውለን ነበር፣ ነገር ግን አልተሳካልንም። ስናገኘቸው አነጋግረን ያለውን ሁኔታ ለማቅረብ እንሞክራለን።

አንድ ከዚህ ጋር ተያያዥነት ያለው ነገር ተነስቷል። የእንግሊዝኛው ቃል ዜኖፎቢያ(xenphobia)ትርጉሙም፣ በባዕዳን መጤዎች ላይ ያነጣጠረ ጥላቻ ነው። ምንም እንኳ እንግዶቻችን ቃሉን ጠርተው "ያ ነው የተፈጸመው" ባይሉም፣ የከዚህ ቀደሙ የዘር ወይም የመጤዎች ጥላቻ ሊጀመር ይሆን? የሚል ስጋታቸውን ሰንዝረዋል። ነገሩ ግን ቁጣ አስነስቷል ብለውናል።

አቶ ደስታ ጉዳዩን ሲገልጹ ዜነፎብያ(xenphobia) በደቡብ አፍሪቃ አለ ብላቹ አውጃቿል በማለት ነው ቁጣው የደረሰው ብለዋል።

የደቡብ አፍሪቃ ካርታ

አቶ ደስታ ያሉትን ባጭሩ ለማስቀመጥ፣ “ይህ ግድያ ዜኖፎቢክ ማለትም "መጤ-ጠል" ነው ወይም አይደለም ለማለት ያስቸግራል። "ነው እንዳንል፣ አገሬው እንዳለፈው ጊዜ በመጤዎች ላይ ሆ ብሎ አልተነሳም። አይደለም እንዳንል ደግሞ ነገሩ በዝርፊያ ላይ ወይም ሱቅን በማቃጠል ላይ ብቻ የተመሰረተ አይደለም፣ ገዳዮቹንም ለመያዝና ወደ ህግ ለማቅረብ የአካባቢው ነዋሪ ሲረባረብ አልታየም፣ ያለ ምንም ዝርፊያ ኢትዮጵያውያኑን በመግደል ላይ ብቻ እንዳተኮረ ተመልክተናል። ስለዚህ ሁኔታውን የሚያጠራው ወደፊት የሚደረገው ምርመራ ብቻ ነው” ነው የሚሉት።

አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ መስቀሌ፣ ሌላው የደርበን ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ ጽ/ቤት ኃላፊ ናቸው። ምንድነው ነገሩ? ይህን በኢትዮጵያውያኑ ላይ የተፈጸመ ግድያ እንዴት ያዩታል? ብለን ጠይቀናቸዋል።

አቶ ኤፍሬም፣ “የኢትዮጵያውያን ግድያ ላይ የአገሬው ሕዝብ ሆ ብሎ ለግድያና ለጥፋት አልተነሳም፣ በፊት ግን ከመንግሥት ጀምሮ ጠቅላላ ሕዝቡ ባንድነት የተነሳበት ሁኔታ ስለነበር ያ ነው ዜኖፎቢያ ወይም "መጤ-ጠል" የሚባለው፤ ይህን የአሁኑ "መጤ-ጠ” ለማለት ግን ይከብደኛል ነው ያሉት።

ለማንኛውም ነገሩ በምርመራ ላይ በመሆኑ እንደተጣራ ውጤቱን እንደገልጸለን ብለዋል አሉ አቶ ኤፍሬም። ከዚህ በተረፈ፣ አቶ ኤፍሬም እንደገለጹልን፤ የኢትዮጵያ ኤምበሲ ባለሥልጣናት ወደ ከተማዋ መግባታቸውን ሰምተዋል፣ ከነገ ጀምሮ አንዳንድ ከደርባን ባለሥልጣናት ጋር የተካሄደውን ውይይት አስመልክተው ያገኙትን እንደሚነግሩን ቃል ገብተውልናል።

ሙሉውን ዝርዝር ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

መጤ-ጠል በበደቡብ አፍሪቃዋ ደርበን
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:30 0:00

XS
SM
MD
LG