በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ኤድስ በሽታ አሁንም ዋናው የሞት ምክንያት መሆኑ ተገለጸ


የኤድስ ህመምተኛ በጆሃንስበርግ በሚገኘው ሄለን ጆሴፍ ሆስፒታል (Helen Joseph Hospital in Johannesburg)
የኤድስ ህመምተኛ በጆሃንስበርግ በሚገኘው ሄለን ጆሴፍ ሆስፒታል (Helen Joseph Hospital in Johannesburg)

ደቡብ አፍሪቃ ከመጀምርያውም ቢሆን ኤችአይቪ/ኤድስ (HIV/AIDS) ተስፋፍቶባት የነበረች ሃገር ስትሆን በሽታው አሁንም ቢሆን ለሞት ስለ መዳረጉ ጉዳይ ብዙም አይነገርም። በመሰረቱ በኤድስ (AIDS) ከሚሞቱት ሰዎች 93 ከመቶ የሚሆኑት በስህተት በሌላ በሽታ እንደሞቱ ተደርጎ እንደሚነገር ታውቋል።

ዓለም አቀፍ የኤድስ መከላከል ማህበር እንደሚለው፣ በእንግሊዝኛ ስሙ አንታይ ሬትሮ ቫይራል (Antiretroviral)የተባለው መድሃኒት ከመጣ ወዲህ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በኤድስ ምክንያት የሚሞቱት ሰዎች ቁጥር ቀንሷል። ይህ መልካሙ ወሬ ሲሆን መጥፎው ወሬ አሁንም ኤድስ ለሰዎች ሞት ዋናው ምክንያት ሆኖ መቀጠሉ ነው።

በርደን ያለው የበሽታ ማዕከል ክፍል ስራ አስኪያጅ ዶክተር ደቢ ብራድሾው ከስራ ባልደረቦቻቸው ጋር ሆነው እአአ ከ 1997 እስከ 2010 ዓ.ም. በነበረው ጊዜ ውስጥ በኦፊሴል ሲነገር የቀየውን የሙታን አሃዝ ተመልክተውል።

"ቡድኔ ኤድስ ወረርሽኝ ከገባበት ጊዜ አንስቶ ላለፉት 15 አመታት ገደማ ሲሰራበት ቆይቷል። በ 2000 ዓ.ም. ገደማ (ከ 15 አመታትት በፊት ማለት ነው ኤችአይቪ (HIV) መዛመት እየጨመረ መሄዱን የተገነዘብነው። በሀገሪቱ ስለሚሞቱት ስዎች የሚቀርበው አሃዝ ታድያ በኤድስ (AIDS)ምክንያት የሚሞቱትን አያሳይም ነበር። ለዚህም ምክንያት የሆነው በኤድስ(AIDS)ስለሞቱት ሰዎች ስለማይነገር ነው" ብለዋል ብራድሾው።

ደቡብ አፍሪቃ ከ15 አመታት በፊት ትልቁን የዓለም የኤድስ (AIDS)ጉባኤን ባስተናገደችበት ወቅት ያኔ የሀገሪቱ ፕረዚዳንት የነበሩት ታቦ እምቤኪ ኤችአይቪ/ኤድስን (HIV/AIDS)እንደሚያስከትል አይቀበሉም ነበር። በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የሳይንስ ጠብበት የታቦ እምቤኪን አቋም ነቅፈው ነበር።

"የኤድስ (AIDS)ተቃዋሚዎች ውዥንብር ይነዙ ስለነበርም ፖለቲካዊ ተግዳሮት መሆኑ አልቀርም። ስለሆነም የኤችአይቪ(HIV)ለሞት ምክንያት መሆኑን ለመገንዘብ ቆርጠን ተነስተን ነበር። ይህን መሰረት በማድረግ ነበር ስለሚሞቱት ሰዎች ጉዳይ የሚከታተል አሰራር ያቋቋምነው" ሲሉም ብራድሾው አስረድተዋል።

የእንግሊዜኛው ክፍል ባልደረባችን ጆ ዲካፑአ ያቀናበረውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች። ሙሉውን ቅንብር ከተያያዘው የድምጽ ፋልይ ያድምጡ።

ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ኤድስ በሽታ አሁንም ዋናው የሞት ምክንያት መሆኑ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:45 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG