አዲስ አበባ —
በሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ታግተው ወደ ደቡብ ሱዳን ከተወሰዱት ኢትዮጵያውያን ውስጥ አስራዘጠኙ መመለሳቸውን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጉትላክ ቱት (Gtluak Tuut) ተናገሩ። ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት ሕፃናቱ የተመለሱት በተደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት ነው። የተቀሩትን ለማስመለስ ጥረቶች እንደቀጠሉም አረጋግጠዋል።
እስክንድር ፍሬው ርዕሰ መስተዳድሩን ጉትላክ ቱት ጋምቤላ ክልል ስልክ በመደወል አነጋግሮ የሚከተለውን ዘግቦአል የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።