በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዐሥራ አራት ኢትዮጵያውያን ትናንት በአሰቃቂ ሁኔታ በጋምቤላ ተገደሉ


የጋምቤላ ካርታ
የጋምቤላ ካርታ

እስከአሁን ባደረግነው ክትትል በትናንትናው ዕለት 14 ኢትዮጵያውያን በደቡብ ሱዳን ስደተኞች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውንና አስከሬኖቻቸው ተለይተው ዛሬ ለዘመድ አዝማድ መላካቸውን ለሆስፒታል ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል። አስክሬን ፍለጋው መቀጠሉ ተነግሯል።

ከጋምቤላ ከተማ በስተምሥራቅ 17 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በሚገኘው ጀዊ የስደተኞች መጠለያ ሠፈር አቅራቢያ በተፈፀመ ድንገተኛ ጥቃት ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ።

እስከአሁን ባደረግነው ክትትል 14 ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውንና አስከሬኖቻቸው ተለይተው ለዘመድ አዝማድ መላካቸውን ለሆስፒታል ቅርበት ያላቸው ምንጮች ገልፀዋል።

የደረሱበት ያልታወቀ ሰዎች በመኖራቸው ፍለጋው በየጫካው መቀጠሉን እማኞቹ ገልፀዋል።

ጽዮን ግርማ ሙሉውን ዘገባ ይዛለች።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ።

ዐሥራ አራት ኢትዮጵያውያን ትናንት በአሰቃቂ ሁኔታ በጋምቤላ ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:02 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG