በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጋምቤላ በታጣቂዎች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 208 መድረሱን ኢትዮጵያ አስታወቀች


በየመሪሌ ጎሳ እና በ ኑዌር ደቡብ ሱዳን ውስጥ ግጭት በተፈጠረበት ጊዜ የልዎ ኑዌር ጎሳ አባል ጠመንጃ ይዞ እ.አ.አ. 2013/ፋይል ፎቶ/
በየመሪሌ ጎሳ እና በ ኑዌር ደቡብ ሱዳን ውስጥ ግጭት በተፈጠረበት ጊዜ የልዎ ኑዌር ጎሳ አባል ጠመንጃ ይዞ እ.አ.አ. 2013/ፋይል ፎቶ/

ኢትዮጵያን ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስነው ድንበር ተሻግረው ጥቃት ባደረሱ የመሪሌ ጎሳ አባላት እንደተገደሉ የታወቀው ሰዎች ቁጥር ከ140 ወደ 208 ማሻቀቡን የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ። ከብት ዘራፊ የመሪሌ ጎሳ ታጣቂዎች 102 ህጻናትን አግተው ወደ ደቡብ ሱዳን ማምራታቸውን የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አስታወቀዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት በሳምንቱ ማብቂያ እንዳስታወቁት ብዙዎቹ ሟቾች ሴቶችና ህጻናት ናቸው። በጋምቤላ ክልል አርብለት ጥቃቱን ማድረሳቸው በኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የተገለጸው የመሪሌ ጎሳ አባላት ናቸው።

የሟቾቹ ቁጥር 208 ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ታገቱ ያሏቸው ህጻናት ቁጥር ከ102-108 ይደርሳል። 75 ሰዎች መቁሰላቸውን የመንግስት ምንጮች ገልጸዋል።

የጋምቤላ ክልልን የሚያሳይ ካርታ /ጉግል ማፕ/
የጋምቤላ ክልልን የሚያሳይ ካርታ /ጉግል ማፕ/

እሁድ ማምሻውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ በቴሌቭዥን ንግግር ያደረጉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ መንግስታቸው በደረሰው ጥቃት ማዘኑን ገልጸው፤ የመሪሌ ጎሳ ታጣቂዎችን ተጠያቂ አድርገዋል።

"በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ስልሳ የሚሆኑ አጥቂዎችን መግደላቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚውኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ አሶሽየት ፕረስ (Associated Press) የዜና ምንጭ አስታውቀዋል። አቶ ጌታቸው አክለውም፤ የኢትዮጵያ ሃይሎች ወደ ደቡብ ሱዳን ተሻግረውም አጥቂዎቹን ሊይሳድዱ እንደሚችሉም አስረድተዋል።

ትናንት ማምሻውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ፤ የኢትዮጵያ የጸጥታ ሃይሎች እየወሰዱት ያለውን ርምጃ ሲያብራሩ፤ የታገቱት 102 ህጻናት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመለሱ ጥረት ተይዟል።" ብለዋል።

የመሪሌ ጎሳ ታጣቂዎች ከደቡብ ሱዳን ድንበር የተሻገሩ መሆኑን የገለጹት

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥቃቱን ያደረሱት ታጣቂዎች ከደቡብ ሱዳን መንግስትም ሆነ አማጺያን ጋር ግንኙነት እንደሌላቸው ጨምረዋል። ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር የጋራ ድንበር ተሻጋሪ የጸጥታ ጥበቃ አሰራር ለመፍጠር ከኢትዮጵያ በኩል ጥያቄ መቅረቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ገልጸዋል።

"ኢትዮጵያ ውስጥ ወደ 300ሽህ የሚጠጉ የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በጋምቤላ ክልል ውስጥ ይገኛሉ" ብለዋል።

በተጨማሪም በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘውን የደቡብ ሱዳን ኤምባሲ ደውለን ለሚመለከተው የኤምባሲ ክፍል ጥያቄውን እናቀርባለን ብለውናል።

ዝርዝሩን ሔኖክ ሰማእግዜር ተከታትሏል።

በጋምቤላ በታጣቂዎች የተገደሉት ሰዎች ቁጥር 208 መድረሱን ኢትዮጵያ አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በክስተቱ ላይ ከዶ/ር ደረጀ ፈይሳ ዶሪም ጋር(Dereje Feyissa Dori) ቃለ-ምልልስ አድርገናል። ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

ቃለ-ምልልስ ከዶ/ር ደረጀ ፈይሳ ዶሪ ጋር
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:57 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG