No media source currently available
በሙረሌ ጎሳ ታጣቂዎች ታግተው ወደ ደቡብ ሱዳን ከተወሰዱት ኢትዮጵያውያን ውስጥ አስራዘጠኙ መመለሳቸውን የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጉትላክ ቱት (Gtluak Tuut) ተናገሩ። ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት ሕፃናቱ የተመለሱት በተደረገው የዲፕሎማሲ ጥረት ነው። የተቀሩትን ለማስመለስ ጥረቶች እንደቀጠሉም አረጋግጠዋል።