በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ ማንዴራ ወረዳ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ፣ ሌሎች ሶስት ሰዎች ቆስለዋል


ኬንያ ውስጥ ማንዴራ ወረዳ
ኬንያ ውስጥ ማንዴራ ወረዳ

ኬንያ ውስጥ ማንዴራ ወረዳ በአንድ መኪና ላይ የመንግስቱ ጦር ሰራዊት ወታደሮች ዛሬ ሰኞ ተኩስ ከፍተው ሁለት ሰዎች ገድለው ሌሎች ሶስት ሰዎች አቆሰሉ።

የማንዴራ ወረዳ ኮሚሽነር ፍሬዴሪክ ሺሲያ ለቪኦኤ የሶማሊኛ ቋንቋ በሰጡት ቃል የጸጥታ ሃይሎቹ መኪናው ላይ ተኩስ የከፈቱት ፈንጂ ጭንዋል ብለው ጠርጥረው መሆኑን አስታውቀዋል።

ዕማኞች እንደሚሉት ግን የተገደሉት ሰዎች ሲቪሎች ናቸው። መኪናቸው ውስጥም ምንም መሳሪያ አልተገኘም። የቆሰሉት ደግሞ በስፍራው የነበሩ ተላላፊዎች ናቸው ብለዋል።

ይህ በዚህ እንዳለ ትናንት ዕሁድ ላፌይ በሚባለው የከተማዋ አካባቢ ሁለት ፖሊሶች ከተገደሉበት ጥቃት ተከትሎ ማንዴራ ውስጥ ከባድ የጸጥታ ጥበቃ እንቅስቃሴ እየተካሄደ መሆኑን ነዋሪዎች ገልጠዋል።

ለዚያ ጥቃት የሶማሊያው ጽንፈኛ ተዋጊ ቡድን አል-ሸባብ ሃላፊነት ወስዷዋል።

የኬኒያ ወታደሮች እአአ በ2011 ዓመተ ምህረት አል-ሸባብን ለመውጋት ሶማሊያ ግዛት ጽንፈኛ እስላማዊው ቡድን ኬኒያ ውስጥ በተደጋጋሚ ጥቃቶችን አድርሷዋል።

ባለፈው ሚያዝያ ወር በማዕከላዊ ኬንያ በጋሪሳ ዩኒቨርስቲ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አንድ መቶ አርባ ስምንት ሰዎች መግደላቸው አይዘነጋም። ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

በኬንያ ማንዴራ ወረዳ ሁለት ሰዎች ሲገደሉ፣ ሌሎች ሶስት ሰዎች ቆስለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:36 0:00

XS
SM
MD
LG