በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያና ኬንያ በኢኮኖሚና ጸጥታ ጉዳይ ስምምነት ተፈራረሙ


ኢትዮጵያና ኬንያ በሞያሌ በኢኮኖሚና ጸጥታ ጉዳይ ስምምነት ተፈራረሙ[
ኢትዮጵያና ኬንያ በሞያሌ በኢኮኖሚና ጸጥታ ጉዳይ ስምምነት ተፈራረሙ[

ኢትዮጵያና ኬንያ በሁለቱ ሀገራት ድምበር ከተማ በሆነችዉ ሞያሌ ዉስጥ በኢኮኖሚና ጸጥታ ጉዳይ ላይ የሚያተኩር ስምምነት ተፈራረሙ። በዚህ የስምምነት ፊርማ ስነ-ሥርዓት ላይም የሁለቱ ሀገራት መሪዎችና ምንስትሮች ተገኝተዋል።

ከ3 ሳምንት በፊት ነበር የኬንያዉ ዴይሊ ኔሽን (Daily Nation) ጋዜጣ የኢትዮጵያ ጸጥታ ኅይሎች የኬንያን ድምበር ጥሰዉ በመግባት 3 የኬንያ ፖሊሶች ህይወት ስላጠፍው እርምጃ የዘገበዉ።

ከዝያም ቦኋላ የኬንያ መንሥግት አካባቢዉን በይበልጥ ለመቆጣጠር የሃገሪቱን የሰራዊት ኅይል ያሰፈረ ሲሆን፡ በኢትዮጵያ መንግሥስት ርምጃ ላይ ተቃውሞ ማሰማቱ የሚታወስ ነዉ።

ነገር ግን በትላንትናዉ ዕለት የሁለቱ ሀገራት መሪዎች የሁለቱ ሀገራት ድምበር ከተማ በሆነችዉ ሞያለ ላይ ግምቱ ወደ 200 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ እኮኖሚንና ጸጥታን ያካተተ ስምምነት ተፈራርመዋል። ይህም ስምምነት ለ5 ዓመታት የሚቆይ ሲሆን በኢትዮ-ኬንያ ድምበር አካባቢ አብዛኛዉን ግዜ ለምከሰተዉ የጸጥታ ችግር መፍትሄ እንደምሆንም ታምኖበታል። በፊርማ ሥነ-ሥርአቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የኬንያ ፕረዘደንት ኡሁሩ ኬንያታ ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት የተረሳዉን አካባቢ ይፋ ያወጣል ብለዋል።

“ይገባናል በርግጥ ይህን አካባቢ ለመለወጥ የምደረገዉ ጥረት ከሩቅ ግብ የምያደርስ ነዉ። በዚህ ድምበር አካባቢ ለሚኖሩ ወገኖችም ግጭት፤ ድህነትና አለመረጋጋት በጣም አስቸግሮዋቸዋል። ትልቁ ስራችንም በተቻለን መጠን ይህንን ግጭት በማስቀረት በዚህ አካባቢ የሚኖሩ የኬንያ የኢትዮጵያ ዜጎች ልክ እንደ ሌሎች የሀገራችን ነዋሪዎች ሰላማዊ ኑሮ እንድኖሩ ማድረግ ነዉ” ብለዋል።

እንደ ያኔዉ የተባበሩት መንግስታት ዘገባ ከሁለት ዓመት በፊት በ2013 በተነሳዉ የጎሳዎች ግጭት 70,000 የምሆኑ የኬኛ ዘጎች የኬኛ ድምበር አልፈዉ ወደ ኢትዮጵያ ተሰደዉ ነበር። በሥነ ሥአራቱ ላይ የኢትዮጵያዊው ጠቅላይ ሚኒስትር ኅይለ ማርያም ደሳለኝም ይህ ስምምነት የአካባቢው ሰዎች ሰላም እንዲያገኙ ያደርጋል ብለዋል በንግግራቸዉ።

“የዚህ ፕሮግራም ጥሩነት፣ ታሪክ በአባቢዉ ነዋሪዎች ላይ ያስቀመጠዉን ችግር መፍታት መቻሉ ነዉ” ብለዋል።

በ200 ሚሊዮን ዶላር የምገመተውንም ስምምነት በኢጋድ (IGAD) እና በየተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ዩኤንዲፒ (UNDP) የሚደገፍ ሲሆን በኬንያ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ተወካይ ናርዶስ በቀለ ቶማስ ሞያሌን ወደ ዱባይ እንለዉጣታለን የሚል ተስፋ አዘል ንግግር ለ ታዳሚዎች አሰምተዋል። በመንግሥት ላይ የምገኘዉ የመርሌ-ሞያለ የመንገድ ፕሮጀክትም በመጪዉ እአአ 2016 እንደምጠናቀቅ የኬኛዉ ፕረዘደንት ኡሁሩኬኛታ አሳዉቀዋል።

በኢትዮጵያ በኩል አቶ ቴዎድሮስ አድኅኖም በኬኛ በኩልም አቻቸዉ ወ/ሮ አሚና ሞሃመድ ናቸው ስምምነቱን የፈረሙት። የአሜርካ ሬድዮ ድምጽ ገልሞ ዳዊት ከናይሮቢ አጠናቅሮ የላከውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ኢትዮጵያና ኬንያ በሞያሌ በኢኮኖሚና ጸጥታ ጉዳይ ስምምነት ተፈራረሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:46 0:00

XS
SM
MD
LG