ሕገ-መንግሥታዊ መብታችን በኢሕአዴግ መንግሥት እየተጣሰ ነው ሲል መድረክ አማረረ
ሕገ-መንግሥታዊ መብታችን በኢሕአዴግ መንግሥት እየተጣሰ ነው ሲል መድረክ አማረረሠላማዊ ሰልፍና ሕዝባዊ ስብሰባ የማድረግ ሕገ-መንግሥታዊ መብታችን በኢሕአዴግ መንግሥት እየተጣሰ ነው ሲል መድረክ አማረረ።
የፓርቲው መሪዎች ዛሬ በሰጡት መግለጫ ሕጋዊና የሰላማዊ ትግል መንገዶች እየተዘጉ ነው ብለዋል፡፡
በተለይ ለመጨረሻው የሠላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያቸው ያገኙት ምላሽ “ማስፈራሪያና መድረክን ለመከፋፈል የታለመ ነው” ብለዋል።
በአርሲ የሚካሄደው ተቃውሞ ከተቀረው ኦሮሚያ የተለየ ነው ይላሉ ጌታቸው ረዳ
የመንግሥት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ።
የመንግሥት የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ሚንስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ በኦሮሚያ ከሚካሄደው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ የታሰሩ፣ ጉዳያቸው ተጣርቶ ወንጀል ያልፈጸሙት ይፈታሉ ብለዋል።
ከመንግሥት ታጣቂዎች ጋር በተካሄደ ግጭት አላግባብ ህይወታቸውን ወይም ንብረታቸውን ላጡ የክልሉ ነዋሪዎች መንግሥት ድጋፍ ለመስጠት መወሰኑንም ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ድርጅት ስለ ግጭቱ ጥናት እያካሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ ሕግ የተላለፉ ታጣቂዎችም ለፍርድ እንደሚቀርቡ ተናግረዋል።
የኦሮምኛ ክፍል ባልደረባችን ጃለኔ ገመዳ ናት አቶ ጌታቸውን ያነጋገረቻቸው እስክንድር ፍሬውም ተጨማሪ አለው። ሙሉውን ዘገባ ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ይጫኑ።