በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በኦሮሚያ ወደ ግጭቶች ያመሩ እንቅስቃሴዎች “ያሳስቡኛል” አለች


ዩናይትድ ስቴትስ በኦሮሚያ ወደ ግጭቶች ያመሩ እንቅስቃሴዎች “ያሳስቡኛል” አለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:18 0:00

ዩናይትድ ስቴትስ በኦሮሚያ ወደ ግጭቶች ያመሩ እንቅስቃሴዎች “ያሳስቡኛል” አለች

“የኢትዮጵያ መንግስት የተቃውሞ ድምጾችን ከማፈን እንዲታቀብ፤ የተለያዩ ማኅበረሰብ ክፍሎች በሰላማዊ መንገድ የመመሰብሰብ፥ የመጻፍና ሃሳብን በነጻ የመግለጥ ጨምሮ በሕገ-መንግስት ለታቀፉ የዜጎች በሙሉ መብቶች ጥበቃ እንዲያደርግ ያቀረብነውን ጥሪ ዳግም እናሰማለን።” ጆን ኪርቢ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ(John Kirby) በትላንቱ መደበኛ ጋዜጣዊ መግለጫቸው በተለይ የኢትዮጵያን ወቅታዊ ሁኔታአስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሠፋ ያለ ዝርዝር ያካተተ ምላሽ ሰጥተዋል።

ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የመጡ ኢትዮጵያውያን አሜሪካውያንበትላንትናው ሰኞ በውጭ ጉዳይ ሚንስትር ደጃፍ ባካሄዱት የተቃውሞ ሰልፍበኦሮሚያ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች ወቅትየተገደሉ ሠዎች ጉዳይ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ የኦባማ አስተዳደርበኢትዮጵያ መንግስት ላይ ግፊት ማድረግ አለበት ሲሉ ጠይቀዋል።

“በተለይ በቅርቡ የተካሄዱትንና በጸጥታ ኃይሎችና በሰልፈኞቹ መካከልየተቀሰቀሱ ብጥብጥ ያዘሉ፥ ወደ ከፉ ግጭቶች ያመሩ መጠነ-ሠፊ የተቃውሞእንቅስቃሴዎች አስመልክቶ በኦሮሚያ ያለው ሁኔታ፥ በግልጽ፤ አሳስቦናል።እያሳሰበንም ይገኛል።” ብለዋል፤ ጆን ኪርቢ

“መንግስት የወሰደው የኃይል እርምጃ ለብዙዎች ሞት፤ የፖለቲካ ፓርቲመሪዎችንና ጋዜጠኞችን ጨምሮ ለብዙዎች መታሰር ምክኒያት ሆኗል። እናምአሳስቦናል፤” ነው፤ ያሉት ቃል አቀባዩ።

በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የዲሞክራሲ፥ የሰብዓዊ ጉዳዮችናየሠራተኞች ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ቶም ማሊንዎስኪ (Tom Malinowski) ባለፈው ወርአዲስ አበባ ላይ ለተካሄደው የአፍሪቃ ሕብረት ጉባኤ የዩናይትድ ስቴትስልዑካንን ይዘው በሄዱበት ወቅት ከኢትዮጵያ መንግስት መሪዎችና ከኦሮሞማኅበረሰብ አባላት ጋር መነጋገራቸውን ጆን ኪርቢ አስታውሰዋል።

የተቃውሞ ሰልፎቹ ከከተሞች ማስፋፊያ እቅድ በላይ መሆናችንን ሁላችንምእንግባባለን፤ ብለን እናምናለን።” ያሉት የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይሚንስቴር ቃል አቀባይ ጆን ኪርቢ አክለውም፤ የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈውጥር ወር መጀመሪያ ማስተር ፕላ (Master Plan) በሚለው የእንግሊዝኛው አጠራር በሥፋትየታወቀ የሚመስለውን ያን የቀደመ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ከተሞች ማስፋፊያእቅዱን ለመሰረዝ ይፋ ያደረፈገበትን “የመጀመሪያው አስፈላጊ እርምጃ፤”ብለውታል።

ዩናይትድ ስቴትስ በኦሮሚያ ወደ ግጭቶች ያመሩ እንቅስቃሴዎች “ያሳስቡኛል” አለች።
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:48 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG