አዲስ አበባ —
የሰው ልጅ በሳይንሳዊ ምርምሮች ካሳካቸው ታላላቅ ተግባሮች አንዱ የሆነው ክትባት፥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎችን ሕይወት ማዳኑን ያስታወሱት የዩናይትድ ስቴትስ የበሽታ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል ዳይሬክተር፥ አዲሱን የዚካ ቫይረስ በተመለከተ ግን እስካሁን መድሃኒት አለመገኘቱን አስታውቀዋል።
ለኢቦላ የተገኘው ክትባት ክትባትም ቫይረሱን ለማስቆምና ለመከላከል የተደረገውን ጥረት አይተካም ብለዋል።
የዓለም የጤና ድርጅት ባለሥልጣናት በበኩላቸው፥ የዚካ ቫይረስ በቁጥጥር ሥር ከመዋሉ በፊት፥ የከፋ ጉዳት ሊያደርስ እንደሚችል አስጠንቅቀዋል።
እስክንድር ፍሬው ከአዲስ አበባ ተከታዩን ዘገባ ልኳል።