በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በቴክሳስ ክፍለ ግዛት “ዚካ” በመባል ለሚታወቀው ቫይረስ የተጋለጠ ሰው መገኘቱ ተዘገበ


የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ድርጅት (CDC) ዲሬክተር ዶ/ር ቶም ፍሪደን “ወደ ላቲን አሜሪካ ከተደረገ ጉዞ ጋር ሳይያያዝ በዩናይትድ ስቴትስ መኖሩ በላቦራቶር ምርመራ የተረጋገጠ የመጀመሪያው የዚካ ቫይረስ ክስተት ነው፤” ብለዋል።

በደቡብ ምዕራብ ዩናይትድ ስቴትሷ የቴክሳስ ክፍለ ግዛት “ዚካ” በመባል ለሚታወቀው ቫይረስ የተጋለጠ ሰው መገኘቱ ተዘገበ። በትላንትናው ዕለት ይፋ የተደረገው ዘገባ እንዳመለከተው፤ በዩናይትድ ስቴትስ በግብረ ሥጋ ግንኙነት አማካኝነት ለቫይረሱ የተጋለጠ ሰው ሲዘገብ ይህ የመጀመሪያው ነው።

“ዚካ” በመባል ለሚታወቀው ቫይረስ የተጋለጡ ቦታዎች የሚያሳይ ካርታ
“ዚካ” በመባል ለሚታወቀው ቫይረስ የተጋለጡ ቦታዎች የሚያሳይ ካርታ

ሕመምተኛው ለ“ዚካ” ቫይረስ የተጋለጡት በቅርቡ ቫይረሱ በሥፋት ከተሰራጨባቸው የላቲን አሜሪካ አገሮች አንዷ ከሆነችው ቬንዝዌላ ደርሰው ከተመለሱና ለቫይረሱ መጋለጣቸው ከተረጋገጠ አንድ ሌላ ሰው ጋር የግብረ-ሥጋ ግንኙነት ከፈጸሙ በኋላ ነው፤ ሲሉ የዳላስ አውራጃ ባለ ሥልጣናት ተናግረዋል።

የአውራጃይቱ ባለ ሥልጣናት ዘግየት ብሎ በቲዊተር አማካኝነት በላኩት ሌላ መልዕክት፤ የተባሉት ሕመምተኛ ራሳቸው በቬንዝዌላ ጉብኝት አድርገው የተመለሱ ናቸው፤ ሲሉ አስተላልፈው ነበር።

በቴክሳስ የዚካ ቫይረስ የመገኘቱ ዜና ትክክለኝነት ያረጋገጠው የዩናይትድ ስቴትስ ብሔራዊ የበሽታዎች መቆጣጠሪያ ድርጅት (CDC) ዲሬክተር ዶ/ር ቶም ፍሪደን (Dr. Tom Frieden) በበኩላቸው በትላንትናው እለት በተመሳሳይ በቲዊተር ባስተላለፉት መልዕክት ቫይረሱ ከቬንዙዌላ ከተመለሱት የፍቅር ጓደኛቸው በግብረ ሥጋ አማካኝነት የተላለፈባቸው ወደ ውጭ አገር ያልተጓዙ መሆናቸውን አመልክተዋል።

ዶ/ር ቶም ፍሪደን በተጨማሪም ለአሜሪካ ድምጽ በላኩት የኢሜል መልዕክት፤ “ወደ ላቲን አሜሪካ ከተደረገ ጉዞ ጋር ሳይያያዝ በዩናይትድ ስቴትስ መኖሩ በላቦራቶር ምርመራ የተረጋገጠ የመጀመሪያው የዚካ ቫይረስ ክስተት ነው፤” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG