ዋሽንግተን ዲሲ —
የዚካ ባይረስ በራሱ እምብዛም አሳሳቢ አይደለም። በትንኝዋ መነደፍ ብዙም ሕመም የማያስከትልና ለሕይወትም የማያሰጋ መሆኑ እየተነገረ ነዉ።
ሆኖም ግን ቫይረሱ አዲስ የተወለዱ ሕጻናት ላይ የአካል መጉዋደል እንደሚያደርስ ታዉቋል። በብራዚል ብቻ እስካሁን አራት ሺህ ህጻናት ላይ የአንጎል አካል ጉድለት ተስተዉሏል።
ቫይረሱ በአጭር ጊዜ ዉስጥ በዓለም ሰለተሰራጨ በመሆኑ የዓለም ጤና ድርጅት አስቸኩዋይ የዓለም ጤና ጠር ሲል አዉጇል።
ለጸነሱ ሴቶች የሚሰጥ ዚካ መከላከያ ክትባት እስካሁን አልተገኘም። ስለዚህ የዓለም ጤና ድርጅት ማህበረሰቦች፣ የጸነሱ ሴቶችን በሽታዉን ከምታስተላልፍ ትንኝ ለመከላከል ዘመቻ እንዲጀምሩ የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር አንተኒ ኮስቴሎ (Anthony Costello)ጥሪ አድርጎል። ሊሳ ሽላይን (Lisa Schlein) ከጄኔቫ የላከችዉን ዘገባ ትዝታ በላቸዉ አጠናቅራለች። የድምጽ ፋይሉን በማጫን ያድምጡ።