ዋሽንግተን ዲሲ —
በአሁኑ ወቅት “የዚካ ወረሽኝን ለመከላከል የተሻለው አማራጭ ራስን በቫይረሱ አስተላፊዋ ትንኝ ከመነደፍ መከላከል ነው፤” ሲል የዓለሙ ጤና ድርጅት WHO አስታወቀ።
ለዚህም ዋናው ምክንያቱ የበሽታውን መከላከያ ክትባት መሥራት ጊዜ የሚጠይቅ በመሆኑ ነው።
ከዩናይትድ ስቴትስና እንዲሁም ከብራዚልና ሌሎች ለቫይረሱ ከተጋለጡ አገሮች የተውጣጡ የጤና ባለሥልጣናት ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የምጣኔ ሃብት ኮምሽንና የማኅበራዊ ጉዳዮች ምክር ቤት በላንትናው ዕለት እንዳስታወቁት ዓለም አቀፍ ጥረት በበሽታው ሥርጭት፥ ቁጥጥርና ጥናት ላይ ነው ያተኮረው።