አዲስ አበባ —
ለዚካ ቫይረስ የሚሰጥ ክትባት ለማግኘት እስከ ሁለት ዓመት ሊወስድ እንደሚችል የገለጡት የUS የበሽታዎች መቆጣጠሪያና መከላከያ ማዕከል CDC ዲሬክተር፤ የባለ ሞያዎች ጥረት ግን መቀጠሉን አስረድተዋል።
ዲሬክተሩ ዶ/ር ቶማስ ፍሪዳን አዲስ አበባ ላይ በመካሄድ ላይ ባለውና በክትባቶች ላይ ባተኮረው የአፍሪቃ የጤና ሚንስትሮች ጉባኤ ላይ ተገኝተዋል።