ዋሽንግተን ዲሲ —
የአለም የጤና ድርጅት የዚካ ቫይረስን መዛመት ለመግታት ያወጣውን ስትራቴጂ ለመተግበር $56 ሚልዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው ገልጿል።
በሽታው በሚወለዱ ህጽናት ላይ የአካል ጉዳት እንደሚያደርስ ታውቋል።
የአለም የጤና ድርጅት ስትራቴጂ ሀገሮች የዚካ ቫይረስንና ታያያዥ በሽታዎን የመከታተል ስራ እንዲያዳብሩ ለመርዳት አጋሮችን፣ ጠበብትንና የገንዘብ ምንጭን ማስተባበር እንደሆነ ዛሬ ገልጿል።
የአለም የጤና ድርጅት የሚያስፈልገውን ያህል ገንዘብ እስከሚያገኝበት ጊዜ ድረስ በሽታውን ለመከላከል የአስቸኳይ ጊዜ ገንዘብ እንደመደበ ጠቁሟል። ገንዘቡ በጤናው ድርጅትና ዚካ ቫይረን በመታገል ተግባር በተሰማሩ አለም አቀፍ አጋሮች መካከል እንደሚከፋፈል አስታውቋል።