በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"መንግሥት ርምጃው ትክክል ነው ብሎ የሚቀጥል ከኾነ፤ ለሚመጣው ችግር ኃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል" አቶ በቀለ ነጋ


የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ

የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ያገረሸው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ፡፡የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለሰጡት አስተያየትም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የአዲስ አበባ እና የፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከአንድ ዓመት ከስድስት ወር በኋላ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ያገረሸው ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ መዋሉን የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ ለአሜሪካ ድምጽ ተናገሩ፡፡ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ለሰጡት አስተያየትም ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ዋና ጸሐፊ አቶ በቀለ ነጋ፤በትናንትናው ዕለት ለአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮ ቃለ ምልልስ የሰጡትን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳን ንግግር አንስተው፤"የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ወክለው የተናገሩት በአንድ ወገን ብቻ የደረሰውን ጥፋት ነው፡፡ በጸጥታ ኃይሉ ላይ ብቻ የደረሰውን በማጉላት፣የሟቾች ቁጥር 50 ተጠግቶ እያለ ያንን ሳይናገሩ ማለፋቸው በጣም ነው ያሳዘነን፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ መንግሥት ለዚህ ጉዳይ መሳሪያ ይዞ በንፁሃን ተማሪዎች ላይ መተኮሱ አግባብ እንዳልሆነ ምንም ያሳዩት ፍንጭ ሳይኖር፣ይብስ ብሎ በዛቻና እንደተለመደው ሰዎችን ማስፈራራትና መግደል መፍትሔ ይኾናል ብለው ማሰባቸው እጅግ በጣም አሳዝኖናል፡፡"ብለዋል፡፡

በተጨማሪም "መንግሥት ወደ ዋናው የሕዝብ ጥያቄ ከመሄድ ይልቅ የቀረበውን ጥያቄ ‹ጸረ ሰላም ነው› በሚል ፍረጃ ውስጥ ነው የሚገባው፡፡" ብለዋል፡፡ አያይዘውም መንግሥት እየኾነ ያለው ነገር እውነት ነው? ወይስ እውነት አይደለም? ይሄ ችግር ደርሷል? አልደረሰም? ሕገ መንግሥታዊ የመብት ጥያቄ ነው? አይደለም? የዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብት መጣስ ጥያቄ ነው፣ አይደለም? በሚል ሊመረምር ፈቃደኛ እንዳልኾነ ገልጸው "አትናገሩ ነው በቃ" ብለዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ስለተፈጠረው ኹኔታም አለኝ ያሉትን መረጃ ጠቅሰው ሲናገሩ፤"በነጆ አካባቢ ሰላማዊ ሰልፎች እና የተቃውሞ ሰልፎች ነበሩ፡፡ አንድ ሰው መሰለኝ የጤና ባለሞያ ሞቷል፡፡ ሆስፒታሎች በቁስለኞች ተጨናንቀዋል፡፡በደምቢ ዶሎና በመቀናጆ ምዕራብ ሸዋም እንደዚሁ አልፎ አልፎ ሰላማዊ ሰልፎች እተካሄዱ ነው፡፡ በዳሌ ዋበራና በተለያዩ ቦታዎች ሰላማዊ ሰልፍ ሲካሄድ መንግሥት አሁንም ሰራዊት አሰልፏል፡፡የሚገርመው ሳተላይት ቴሌቭዥን የሚያዩበትን ዲሽ ወታደሩ ከጣሪያ ላይ እያወረደ ይወስዳል የሚል መረጃ ነው ያለን፡፡” ብለዋል፡፡

አያይዘውም፤"መንገደኛ እየተደበደበ ነው፣በሰላም ወጥቶ መግባት አልተቻለም፡፡ መደብደብ ነው፣ ተኩሶ መግደል ነው፡፡ አሁን ለምሳሌ ደንቢዶሎ ላይ የተገደለው ሰውዬ ከቤቱ ተጠርቶ ነው መንገድ ላይ የተገደለው፡፡መንግሥት ጉዳዩን እንደዚህ ዐይነት አስከፊ ወደኾነ ኹኔታ ላይ እየወሰደው ነው ያለው፡፡ መንግሥት ከዚህ ድርጊት በመቆጠብ ወታደሮችን ከሰላማዊ አካባቢዎች በማስወጣት ሕዝቡ ሰላም እንዲፈጥር መንገድ መክፈት አለበት እንጂ ይሄንን ርምጃ ትክክል ነው ብሎ የሚቀጥል ከኾነ፤ ለሚመጣው ችግር ኃላፊነት መውሰድ ይኖርበታል"ብለዋል፡፡

ቃለ ምልልሱን ከተያያዘው ድምጽ ያድምጡ፡፡

ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG