በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል ተቃዉሞ ሰልፎች ከ30 በላይ ሰዎች ተገደሉ


በኦሮሚያ ክልል ሲደረጉ በቆዩ የተቀዉሞ ሰልፎች የተገደሉ ዜጎች ቁጥር ከ30 በላይ መድረሱን ዛሬ የኢትዮኢጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ገለጸ። የቆሰሉትና የታሰሩትም በመቶዎች እንደሚቆጠሩ አስታዉቋል።

መድረክ አሁን ኦሮሚያ ዉስጥ የሚካሄደዉ ተቃዉሞና መንግስት ለማስቆም እየወሰደ ያለዉ እርምጃ አዉግዞ በፍጥነት እንዲቆም ጠይቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከኦሮሚያ ክልል ጋር ያላት ግንኙነትም በሕገ መንግስቱ ድንጋጌ መሰረት እንዲተገበር በማለት ገልጿል። የሰዉ ሕይወት የጠፋበት ግጭት ይረግብ ዘንድም ጊዜአዊና ዘላቂ መፍትሔዎችን ጠቁሟል።

መሰስካቸዉ አመሃ ከላከዉ ዘገባ ዝርዝሩን ያድምጡ።

በኦሮሚያ ክልል ተቃዉሞ ሰልፎች ከ30 በላይ ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:33 0:00

XS
SM
MD
LG