በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፎን ተከትሎ፡ ከ40 በላይ ሞቱ (ኦፌኮ) 32 (መድረክ) አምስት (መንግስት)


የኢትዮጵያ የኮሚውኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው - ፋይል ፎቶ [ከኤኤፍፒ ቪድዮ የተገኘ ፎቶ/AFP]
የኢትዮጵያ የኮሚውኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው - ፋይል ፎቶ [ከኤኤፍፒ ቪድዮ የተገኘ ፎቶ/AFP]

“ከአራት በላይ የፖሊስ ባልደረቦች ተገድለዋል” የኢትዮጵያ መንግስት መግለጫ

“በኦሮሚያ ግጭቶች 5ሰዎች ተገድለዋል፤ በግንደበረት ከ4በላይ የፖሊስ ባልደረቦች ተገድለዋል” ይላል የኢትዮጵያ መንግስት መንግስት። ተቃዋሚው የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ደግሞ ከ40 በላይ ይላል።

ኦፌኮ አባል የሆነበት መድረክ ባወጣው መግለጫ የ32 ሰዎችን ስም ዝርዝር ከነመኖሪያ አድራሻቸው ይፋ አድርጓል። በመቶዎች መቁሰላቸውንም አስታውቋል። ዛሬ ማምሻውን የኢትዮጵያ መንግስ ከአራት በላይ የፖሊስ ባልደረቦች “እጅግ አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ” መገደላቸውን ጨምሮ አስታውቋል።

በኦሮሚያ ክልል የተቀሰቀሱ ሰላማዊ ሰልፎችን አስመልክቶ የኢትዮጵያ የኮሚውኒኬሽንስ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ማምሻውን ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የሰልፈኞቹን ጥያቄና ተያይዞ የተከሰተውን ሁከትና ግድያ አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። ቃለ ምልልሱን ከዚህ በታች ካለው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

የኦሮሚያ ሰላማዊ ሰልፎን ተከትሎ፡ ከ40 በላይ ሞቱ (ኦፌኮ) 32 (መድረክ) አምስት (መንግስት)
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:59 0:00

XS
SM
MD
LG