በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፍሪካና አውሮፓ ፍልሰተኞች በሀገራቸው በምጣኔ ሀብት ተሳትፏቸውን ለመጨመር ይቻላቸው ይሆን?


ፍልሰተኞች በመርከብ በጣልያን ባህር ዳር እ.አ.አ. 2016
ፍልሰተኞች በመርከብ በጣልያን ባህር ዳር እ.አ.አ. 2016

ከአርባ የሚበልጡ መሪዎችና በርካታ ወኪሎች የተገኙበት የአፍሪካ-ጣሊያን ጉባዔ አትኩሮት፤ በምጣኔ ሀብት እድገት ፍልሰትን በመከላከል ላይ ያተኮረ ሆኗል። ዘለቄታ ያለው ልማት በማምጣትና ለፍልሰተኞች በየሀገሮቻቸው የስራ እድሎችን በመፍጠር፤ ወደ አውሮፓ በአስቸጋሪ መንገዶች የሚደረገውን ፍልሰት ለማስቆም የጋራ ውይይት አካሂደዋል።

ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ አውሮፓ የሚፈልሱና የሚሰደዱ አፍሪካዊያንን ጉዳይ አስመልክቶ ለመወያየት የጣሊያን መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ከ50 የሚበልጡ የአፍሪካ ሀገሮች ባለስልጣናት ጋር ረቡዕ እለት ውይይት ሲያደርጉ ውለዋል።

ዘለቄታ ያለው ልማት በማምጣትና ለፍልሰተኞች በየሀገሮቻቸው የስራ እድሎችን በመፍጠር፤ ወደ አውሮፓ በአስቸጋሪ መንገዶች የሚደረገውን ፍልሰት ለማስቆም የጋራ ውይይት አካሂደዋል። ከአርባ የሚበልጡ መሪዎችና በርካታ ወኪሎች የተገኙበት የአፍሪካ-ጣሊያን ጉባዔ አትኩሮት፤ በምጣኔ ሀብት እድገት ፍልሰትን በመከላከል ላይ ያተኮረ ሆኗል።

በዚህ በያዝንው ዓመት ከ30ሽህ በላይ ስደተኞች ወደ አውሮፓ በሰሜን አፍሪካ በኩል መግባታቸው የጣሊያን መንግስትንና የአውሮፓ ሀገሮችን ያሳሳበ ጉዳይ ሆኗል። የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፓውሎ ጄንቲሎኒ በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር፤ የጋራ የምጣኔ ሀብት ልማት ስራዎች የሚሰሩበትን እቅድ ይፋ ማድረጋቸውን በሮም ዘገባ በማቅረብ የምትገኘው ጆሴፊን ማኬና ገልጻለች።

“የጣልያን መንግስት ለአውሮፓ ህብረት ያቀረበው እቅድ አለ፣ ማለትም በአፍሪካ በርካታ የስራ እድሎችን የሚከፍቱ፣ የአፍሪካ የምጣኔ ሃብትን ሊያጎለብቱ የሚችሉና አፍሪካውያኑን ከመሰደድ ይልቅ በሃገራቸው ሰርተው ስኬታማ የሚሆኑበትን መንገድ የሚያሳይ ነው። በእርግጥ እቅዱን ለመተግበር ከፍተኛ የገንዘብ ፍሰትን ይጠይቃል። የአፍሪካ ህብረትም ጊዜያዊ የገንዘብ እርዳታን ለዚሁ ቢመድብም ቀጣይነት ስለመኖሩ ግን የተረጋገጠ አይደለም።” የጣሊያን መንግስት ለአውሮፓ ህብረት በተለይ የከባቢ አየር ለውጥን ለመከላከል፣ አልፎም በአፍሪካ አነስተኛና ጥቃቅን የንግድ ተቋማት የሚስፋፉበትና፣ በስራ ተሰማርተው ስራ ለመፍጠር የሚችሉበትን መንገድ ለማመቻቸት በፖሊሲና በገንዝብ እርዳታ ስራ እንዲጀመር ጠይቋል።

የአውሮፓ መሪዎች በጉዳዩ ቢስማሙም፤ ገንዘቡ በማንና እንዴት እንደሚከፈል፤ ወይንም ደግሞ በርሃ-ግብሮቹ እንዴት እንደሚተገበሩ፤ በአግባቡ የተጠና እቅድና የአሰራር አግባብ የለም። አፍሪካ እድሚያቸው ከ15-24 የሆነው ህዝቧ 63 ከመቶ የህዝቡን ብዛት ይወክላል።

በስራ ከተሰማራ ሃይል ውስጥ ደግሞ 33ከመቶ የሆነ ድርሻ አላቸው። የአፍሪካ አህጉር በየዓመቱ 10 ሚሊዮን አዳዲስ የስራ እድሎችን መፍጠር ለነዚህ ወጣቶች መፍጠር አለባት። ለዚህ አዲስ ትውልድ በፍጥነት የስራ እድል መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን የአፍሪካ ሀገሮች ለራሳቸው መረጋጋትና ደህንነት ሲሉ የሚፈልጉት ጉዳይ ነው። ግብርናን ያማከለ የኢንዱስትሪና ቴክኖሎጂ እድገት፤ በወጣት በስራ ፈጠራ ካልታገዘ ውጤቱ ስደት፣ ፍልሰትና አለመረጋጋት ይሆናል።

አፍሪካና አውሮፓ ፍልሰተኞች በሀገራቸው በምጣኔ ሀብት ተሳትፏቸውን ለመጨመር ይቻላቸው ይሆን?
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:24 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG