በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፈረንሳይ ወደብ በካሊ ደሴት አቅራቢያ በሚኖሩ ስደተኞች መካከል በተነሳ ጥል ሃያ ሰው ቆሰለ


በፈረንሳይ ወደብ በካሌ የስደተኞች መኖሪያ አካባቢ በአፍጋኒዎችና አፍሪካውያን መካከል በተፈጠረ ውዝግብ ከ20 በላይ የሚሆኑ ቆስለዋል፡፡

በፈረንሳይ ወደብ በካሌ የስደተኞች መኖሪያ አካባቢ በአፍጋኒዎችና አፍሪካውያን መካከል በተፈጠረ ውዝግብ ከ20 በላይ የሚሆኑ ቆስለዋል፡፡

2መቶ የሚሆኑ ስደተኞች ከትናት በስቲያ ሰኞ ጀምሮ እስከ ትናንት ማክሰኞ ማምሻውን በዘለቀ ግጭት በርካቶች የቆሰሊ ሲሆን ስደተኞች ስለትነት ያላቸው የብረት ዕቃዎችን እና እንጨቶችን ይዘው እንደነበር ተገልጿል፡፡

በካሊስ የሚገኘው የአካባቢ ባለሥልጣናት እንደገለፁት ሃያ ሰዎች የቆሰሉ ሲሆን አምስት ሰዎች በቁጥጥር ሥር እንደዋሉም ተናግረዋል፡፡

በፈረንሳይ ወደብ በካሊ ደሴት አቅራቢያ በሚኖሩ ስደተኞች መካከል በተነሳ ጥል ሃያ ሰው ቆስሏል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:27 0:00

ግጭቱ የተነሳው በአካባቢ የነበረ አንድ የበጎ አድራጎት ድርጅት /የአቤርጅስ ማይግራንትስ/ በነፃ ምግብ ስርጭት ወቅት ሲሆን በመጠጥ ኃይል የተነሳሱ ስደተኞች፣ ለፀቡ መነሻ ምክንያት መሆናቸው ተጠቁሟል፡፡

ካሊስ ለበርካታ ስደተኞች ወደ ብሪታንያ ለመጓዝእና ወደሌሎች ሀገራት ለመጓዝ አጭር መሸጋገሪያ ስፍራ ነው፡፡

የአካባቢው ባለስልጣናትና የፈረንሳይ መንግሥት በወደቡ አካባቢ የስደተኛ ካምፖች እንዳይቆሽሹ ለማገድ በቅርቡ መሰረታዊ የንፅህና መስጫ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተገደዋል፣ የፈረንሳይ መንግሥት የስደተኞቹን መሰረታዊ ፍላጎት ባለማሟላቱ ዒሰብአዊ፣ አዋራጅ ሁኔታ ውስጥ እንዲኖሩ ተገደዋል ብሏል፡፡ በቅርቡ አንድ ፍርድ ቤት በአካባቢው የሚገኙ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችም የፈረንሳይ መንግሥትን በቸልተኝነት ያወግዛሉ፡፡

ይሁን እንጂ በካሊ አካባቢ በፖሊስ እና በስደተኞች መካከል ግጭቶች መከሰት የተለመደ ችግር ሲሆን አብዛኛውን ጊዜ ወደ ብሪታንያ በሚገቡ የጭነት መኪናዎች ላይ ስደተኞች ጉዳት ለመጣል ሙከራዎችን ሲያደርጉ ይስተዋላል፡፡

በሀምሌ ወር መጀመሪያ በአፍሪካውያን ስደተኞች ማለትም በኤርትራውያን እና ኢትዮጵያውያን መካከል ግጭቶች ተከስቶ እንደነበርም አሥራ ስድስት ስዎችም ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል፡፡

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG