የዩናይትድ ስቴትስ የነፃነት ቀን ሲከበር በየዓመቱ የተለያዩ ዝግጅቶች ይሰናዳሉ ብሔራዊው ቤተ- መዛግብት የእነዚያ ዝግጅቶች ባለቤት ነው፡፡ ከዚህ ዓመት ክንዋኔዎች መካከል “አሜሪካን መጠገን” ተብሎ የተሰየመው ኤግዚቢሽን ጊዜውን የመጠነ ይመስላል፡፡ ይህ ኤግዚቢሽን አሜሪካ የምትገዛበትን፤ መሠረታዊ መርሆች እና የቀደሙ እውነታዎችን ያቀፈ እምቅ ሕገ መንግሥቷን ለመለወጥ የተደረጉ በሺሆች የሚቆጠሩ የከሸፉ ጥረቶችና ሙከራዎችን ያሳያል፡፡
አሜሪካውያን ሀገራቸው ዩናይትድ ስቴትስ የተመሰረተችበትን ዕለት በየዓመቱ በዚህ ዕለት እኤአ ጁላይ - 4 ያከብሩታል። ዕለቱ ብሔራዊ የዓመት በዓል ነው። በየቦታው ክብረ በዓላት ይካሄዳሉ፡፡ ሰማዩ በርችት ይንቆጠቆጣል። የቪኦኤው ኣራሽ አራብሳዲ ዋሺንግተን በሚገኘው ብሔራዊ ሞል ተዘዋውሮ ሰዎችን “ዕለቱ ደስ የሚል ክብረ በዓል ነው፣ እንዴት ነው የምታከብሩት?” ብሎ በመጠያየቅ ያጠናቀረውን ዘገባ ቆንጅት ታየ ታቀርበዋለች።
የኢትዮጵያ ስፖርት ፌደሬሽን በሰሜን አሜሪካ 34ኛው ዓመታዊ የስፖርት እና የባህል ዝግጅት በሲያትል ዋሽንግተን እየተካሄደ ነው፡፡
የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑኤል ማክሮን በአፍሪካ የሳህል አካባቢ ሃገሮች ሽብርተኝነትን ለሚዋጉ ሃገሮች ፈረንሳይ ወታደራዊና የገንዘብ ዕርዳታ እንደምትሰጥ አስታወቁ። የፈረንሳዩ ፕሬዚደንት በማሊ አምስት ሀገሮች ለሚሳተፉበት ክልልላዊ ፀረ ሽብርተኛ ሠራዊት የምዕራባውያንን ድጋፍ ለማጠናከር የታለመ ጉብኝት አድርገዋል።
በአንዳንድ ሀገራት ያሉ የሰላምና የፀጥታ ጉዳዮች አሳሳቢ መሆናቸውን ቀጥለዋ ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ተናገሩ፡፡
ካታር ከጎረቤቶቿ ጋር ለገባችበት የዲፕሎማሲ ቀውስ መፍትኄ ለመፈለግ እየተንቀሳቀሱ ያሉት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሬክስ ቲለርሰን ከካታርና ከቀሩት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ከትናንት በተስያ ማክሰኞ ተገናኝተው መክረዋል፡፡
ጣሊያን ከሰሜን አፍሪካ ሜዲቲራኒያንን ባሕር አቋርጠው በየቀኑ የሚጎርፉ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ፍልሠተኞችን መቀበል በቀጠለችበት በአሁኑ ወቅት የአውሮፓ ሕብረት ሊረዳት ቃል ገብቷል፡፡ ጣሊያን ፍልሠተኞቹን ያሳፈሩ የውጭ ሀገር ጀልባዎች ወደ ወደ ወደቦቿ አንዳይገቡ ለማገድ ዝታለች፡፡ ከአለፈው ጥር ወር ጀምሮ 80 ሺሕ የሚደርሱ በደህና ገብተዋል፤ ከ2 ሺሕ በላይ የሚሆኑት ግን አልቀዋል ተብሏል፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰዎችን ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ማሸጋገርን አስመልክቶ ባወጣው ዓመታዊ ዘገባ ከዓለም የከፋ በደል የፈፀሙ ያላቸውን 23 ሀገሮች ዘርዝሯል፡፡ ቻይና ከበፊቱ ዝቅ ብላ ከሰሜን ኮርያና ከሶርያ ጋር መሰለፏን ተመልክቷል።
ሰንሰለት ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ የድራማው ደራሲና ዳይሬክተር ተመስገን አፈወርቅ እና ሌላው የፊልሙ ዳይሬክተር ቴዎድሮስ ለገሰ ከአሜሪካ ድምፁ አሉላ ከበደ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ። ቪዲዮ ኤዲቲንግ አበባየሁ ገበያው
ከፈረንሳይ በስተቀር አብዛኞቹ የአውሮፓ ጦር ኃይሎች ለየትኛውም ወታደራዊ ጣልቃ ገብ ሥራ የተሰናዱ አይደሉም።
ኢትዮጵያ ውስጥ የአደጋ ጊዜ “ምግብ ክምችት እየተሟጠጠ ነው” ሲሉ ግብረ-ሰናይ ድርጅቶች እያስታወቁ ነው፡፡
የዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ የምርጫ ዘመቻቸው ከሩሲያ ጋር “አለው” የተባለውን ግንኙነት ምርመራ እንዲያቋርጥ ሰፊና ተደጋጋሚ ጥረቶች በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኩል ተካሂደውበታል ሲሉ የቀድሞው የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ጄምስ ኮሜ ተናግረዋል።
የቀድሞው የዩናይትድ ስቴትስ የፌዴራሉ ምርመራ ቢሮ ዳይሬክተር ጄምስ ኮሜ ዛሬ በሴኔቱ የደኅንነት ኮሚቴ ፊት ቀርበው የምሥክርነት ቃላቸውን ሰጡ፡፡
ለሦስት ቀናት ለሥራ ጉብኝት ወደ መካከለኛው ምሥራቅ ያቀኑት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ በትናንትናው ዕለት የእስራኤልን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታናሁን አግኝተው አነጋገሩ፡፡ ጠቅላይ ሚንስትሩ በያድ ቫሻም እልቂት የተፈፀመባቸው ሕዝቦች መታሰቢያ የአበባ ጉንጉን አኑረዋል፡፡
የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት በበኩላቸው በአሰራራቸው ላይ መሰናክል እንደገጠማቸው እየገለፁ አገልግሎት ፈልገው ወደ ኢንተርኔት ካፌው የሚያመሩ ሰዎች በተለይም የቪዛ ፕሮሰስ፣ ከተለያዩ ዓለማት ጋር የሥራ ግንኙነት የሚያደርጉ ሰዎች እየተጎዱ ነው፡፡
የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር ለውጭ ጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ የኢንተርኔት አገልግሎት የተዘጋው የተፈታኝ ተማሪዎችን ጥቅም ለመጠበቅ ነው ሲል የመንግሥት ኮምየኒኬሽንስ ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡
የቀድሞው የቅዱስ ጊዎርጊስ፣ የመድህንና የቡና ክለቦች የብሄራዊ ቲም ታዋቂ ተጫዋች አሰግድ ተስፋዬ የቀብር ሥነ ስርዓት በሳሊተ ምህረት ተፈፅሟል፡፡
ሕይወትና ሙዚቃ በጥበባዊ ሥራዎቹ ለማኅበረሠብ ባበረከተው አጽተዋፅፆ ከዩናይትድ ስቴትሱ የኢትዮጵያውያን የሽልማት ድርጅት የተሰጠ ክብርና ዕውቅናም ከቴዲ ጋር የምናደራው ወግ አካል ነው።
እአአ በ2016 የአፍሪካ የኢኮኖሚ እድገት ከ2015 ግማሽ ያህል ሊሆን አለማቻሉ ይፋ የተደረገ ሪፖርት አመለከተ፡፡ የተዳከመው የዓለም የኢኮኖሚ ሁኔታ አነስተኛ የነዳጅ ዘይትና የሽቀጦች ዋጋ፣ ድርቅ የፀጥታ ጉዳይ እና በአንዳንድ የአፍሪካ ክፍሎች የታየው የፖለቲካ አለመረጋጋት ከምክንያቶቹ መካከል ተጠቅሷል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ