ከሽሬ እንደሥላሴ አካባቢ ለመውጣት የሞከሩ የመከላከያ ሠራዊት መኪኖች ሕዝብ አናስወጣም ብሎ በስታድዮም እንዳገታቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል፡፡
የኢትዮጵያና የኤርትራ የዛላንበሳ ድንበር ዛሬ መዘጋቱን የትግራይ ክልል የጉሎ መኸዳ ወረዳ የፀጥታ ኃላፊ ገልፀዋል፡፡
የትግራይ ተወላጅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለደኅንነታችን እንሰጋለን ሲሉ ወደ ሌሎች የሃገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይ ወደ አማራ ክልል አንሄድም፣ እዚሁ ክልላችን ውስጥ እንመደብ ሲሉ በቅርቡ መቀሌ ከተማ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተዘግቧል። በትምህርት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ ስለዚሁ ተጠይቀው፣ “በቂ ዝግጅት ስለተደረገ የሚያስፈራ ምክንያት የለም” ብለዋል።
የትግራይ ተወላጅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለደኅንነታችን እንሰጋለን ሲሉ ወደ ሌሎች የሃገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች በተለይ ወደ አማራ ክልል አንሄድም፣ እዚሁ ክልላችን ውስጥ እንመደብ ሲሉ በቅርቡ መቀሌ ከተማ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄዳቸው ተዘግቧል።
የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ስድስት ሴቶች ያሉበትን ዘጠኝ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን ሾመ።
የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጭ ግንባር - ሕወሓት አሥራ ሦስተኛ መደበኛ ጉባዔውን የፊታችን ማክሰኞ፤ መስከረም 16/2011 ዓ.ም. እንደሚጀምር አስታውቋል።
በኢትዮጵያና በኤርትራ የሰላም ስምምነት ከተደረገ በኋላ በሁለቱ አገሮች መካከል ያለው ድንበር ፈርሶ የእርስ በእርስ ግብይት ተጀምሯል።
ለረጂም ጊዜ በታይህታይ አድያቦ በወረዳ በሽራሮ ከተማ የነበረው በመከላከያ ሠራዊት በመሐል ሀገር ያለ የፀጥታ ሁኔታን ለማረጋጋት በሚል ዛሬ ከሽራሮ ከተማ መውጣቱን የታይህታይ አዲያቦ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ሙሉ መብራቱ ገልጸዋል፡፡
ትግራይ ክልል ውስጥ መሆኒ ከተማ ላይ አንድ ድልድይ ሥር ተቀጣጣይ ፈንጂ እንደተገኘ የራያና አዘቦ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ተናግረዋል።
የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን አሰታወቁ፡፡ የትግራይ ክልል መስተዳድርና በግላቸው ቤተሰቦቻቸውን ለማገዝ እንደወሰኑ ለጋዜጠኞች አስታወቁ፡፡
የትግራይ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በኢንጂነር ስመኘው በቀለ ሞት የተሰማቸውን ሀዘን አሰታወቁ፡፡
ኢትዮጵያ ውስጥ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች አለመረጋጋትና የእሣት ቃጠሎ እየደረሰ መሆኑ ይዘገባል።
ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየ የትግራይ አስተዳደር ተጨባጭ ሁኔታ የምክክር መድረክ ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡
የምሁራን ዓለምአቀፍ ጉባዔ ከነገ ጀምሮ በመቀሌ ከተማ እንደሚካሄድ ተገለፀ።
ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን በሁለቱም ሀገሮች መካከል የተጀመረው የሰላም ስምምነት ጎዞ፤ እንዲሁም በጠ/ሚኒስትር አብይ አሕመድ እና በፕሬዚዳንት ኢሳያይ አፈወርቂ የተፈረሙ ስምምነቶች፣ እንዳበረታታቸው እና ተስፋ እንደሰጣቸው እየገለፁ ነው።
በመቀሌ ከተማ ዛሬ በብዙ ሺህ የሚቆጠር ሕዝብ በተገኘበት የሰማዕታት ቀን ታስቦ ውሏል።
የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርስን ስምምነትና የሄግን የድንበር ኮሚሽን ውሣኔ እንደሚቀበል ማስታወቁን በመቃወም አረና ለሉአላዊነትና ለዴሞክራሲ የጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬ መቀሌ ላይ ተካሂዷል።
የአልጀርስን ስምምነት የኢትዮ ኤርትራ የድንበር ኮሚሽንን ውሣኔ እንደሚቀበል የኢህአዴግን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የደረሰበትን አቋም በመቃወም በድንበሩ አካባቢ ያለው የኢሮብ ተወላጆችና የአዲግራት ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል፡፡
በአዲሱ ጠ/ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ መሾምና ባደረጉት ንግግር ላይ ከአዲስ አበባ እና ከመቀሌ ዘጋቢዎቻችን ከዚህም ከዚያም ከሕዝብ የሰበሰቧቸውን አስተያየቶች አድርሰውናል፡፡
ተጨማሪ ይጫኑ