በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ቤርሣቤህ ውስጥ የተገደለው ኤርትራዊ ጉዳይ ዓለምን እያነጋገረ ነው


ቤርሣቤህ ውስጥ የተገደለው ኤርትራዊ ወልደሚካዔል ዘርኦም
ቤርሣቤህ ውስጥ የተገደለው ኤርትራዊ ወልደሚካዔል ዘርኦም

እሥራኤል ውስጥ ትናንት የተገደለው ኤርትራዊ የሞተው በተተኮሰበት ጥይት ምክንያት መሆኑን ቀዶ ሕክምናውን የሠሩት ሃኪም ገልፀዋል፡፡

ቤርሣቤህ ውስጥ የተገደለው ኤርትራዊ ጉዳይ ዓለምን እያነጋገረ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:04 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

እሥራኤል ውስጥ ትናንት የተገደለው ኤርትራዊ የሞተው በተተኮሰበት ጥይት ምክንያት መሆኑን ቀዶ ሕክምናውን የሠሩት ሃኪም ገልፀዋል፡፡

እሥራኤል ውስጥ ይኖርና ይሠራ የነበረው ኤርትራዊ ፍልሰተኛ ወልደሚካዔል ዘርኦም ላየ በቤርሣቤህ ከተማ አውቶቡስ ማቆሚያ ላይ በፖሊስ በተተኮሰበት ጥይት እና በአባባቢው በነበሩ ሰዎች በደረሰበት ድብደባ ምክንያት ሕይወቱ ማለፉን የሚያሣዩ ዘገባዎች በዓለም መገናኛ ብዙኃን እየተናኙ ነው፡፡

እዚያው ሥፍራ ላይ ቀደም ሰል አንድ ሌላ ሰው ተኩስ ከፍቶ አንድ እሥራዔላዊ ወታደር ገድሎ ሌሎች አሥር ሰዎችን ማቆሰሉን የጠቆመው የእሥራኤል ፖሊስ ወልደሚካዔል ላይ የተኮሰበት ያንን ተጠርጣሪ መስሎት በስህተት እንደነበር ገልጿል፡፡

“በስህተት የተፈፀመ” የተባለው የወልደሚካዔል ግድያ የእሥራዔሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁንና የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትን ጨምሮ የተለያዩ ዓለምአቀፍ አካላት በጉዳዩ ወዲያ ጣልቃ እንዲገቡና ምላሾችን እንዲሰጡ አስገድዷል፡፡

የወልደሚካዔልን ሕይወት ለማትረፍ ጥረት ያረደጉት የሶሮካ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ዮሃናን ባይዘል ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ወልደሚካዔል ሆስፒታል የደረሰው በሕይወት ቢሆንም ለሦስት ሰዓት ያህል የቆየ የቀዶ ሕክምና ሙከራና መረባረብ ቢደገግለትም በደረሰበት ከባድ ጉዳት ምክንያት ማትረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

“ደረቱና ሆዱ ላይ ባጋጠሙት ቁስለቶች ለባድ ጉዳት ላይ ወድቋል፤ ሕይወቱን ለሕልፈት ያደረሰው ግን የመቱት ጥይቶች ያመጡበት ጉዳቶች ናቸው” ብለዋል ዶ/ር ባይዘል፡፡

የእግሩ አጥንት መሰበሩን፤ ሆስፒታል ከመድረሱ በፊትም ብዙ ደም የፈሰሰው በመሆኑም ማትረፍ አለመቻሉን ገልፀዋል፡፡

እሥራኤል ውስጥ ያለው ሁኔታ እጅግ ውጥረት የበዛበት መሆኑን ዶ/ር ባይዘል ጠቁመው ግድያውን ፈፅሞ የማይገባ ሲሉ የመረረ ኀዘን እየተሰማቸው እንደሆነ ደጋግመው ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG