በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሜዲቴራኒያኑ ‘ዘመቻ ሶፍያ’ በልጇ የተሰየመው ሶማሊያዊት ታሪኳን ትናገራለች


ባለፈው ነኀሴ ሜዲቴራኒያን ባህርን ለመሻገር ከተሣፈረችበት ጀልባ ባወጣት የጀርመን የባህር ኃይል መርከብ ላይ የተገላገለችው ሶማሊያዊት ስደተኛ ፍልሰተኞችን በሚያሸጋግረው ጀልባ ላይ የተሣፈርኩት “ከነፅንሴ ብሞትም ልሙት ብዬ ነው” ብላለች።

ሰላሣ ሦስት ዓመት ዕድሜዋ ላይ የምትገኘው ራህማ አሊ በእርግዝናዋ ወቅትና በኋላም በጀርመኑ የባህር ኃይል መርከብ ላይ ምጥ ሲይዛት ስላሳለፈችው ከባድ ሥቃይ ስትገልፅ “ጉዞው እጅግ በጣም አደገኛ ነበር፤ ልጄን ግን በምንም ዓይነት ሊብያ ውስጥ መውለድ አልፈለግኩም” ብላለች።

“…ዞር ብሎብኝ ነበር፤ አምስት ወር ሙሉ ስጓዝ ስለነበረ ደክሞኛል፡፡ ልጄን ሊብያ አልወልድም፤ ብንሞትም እንሙት ብዬ ነው የተነሣሁት … ያለችው ራህማ … ሊብያ ውስጥ ያሣለፍኩት ሁኔታ ከባህር ጉዞው የባሰ ነበር” ብላለች።

አሰቃቂ ከምትላቸው አጋጣሚዎች አንዱን እንዲህ ታስታውሳለች …

"አንዷ ነፍሰ ጡር ሴት ሊቢያ ጠረፍ ላይ አንዱ ጀልባ ላይ ልትሣፈር ስትል ምጥ ያዛት፤ ወለደችና እዚያው ሞተች፤ ልጇም ወዲያው ሞተ፡፡ ሌላም እርጉዝ ሴት ጀልባው ላይ ነበረች። እርሷ ግን በህይወት አውሮፓ ደርሳለች” ብላለች።

የሜዲቴራኒያኑ ‘ዘመቻ ሶፍያ’ በልጇ የተሰየመው ሶማሊያዊት ታሪኳን ትናገራለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:56 0:00

እርሷና ሌሎች አብረዋት የነበሩ አራት መቶ ሰላሣ አምስት ስደተኞች የጀርመኑ ባህር ኃይል መርከብ ደርሶ ካተረፋቸው በኋላ ነው ራህማ አሊ መርከቡ ላይ ምጥ የጀመራት።

ራህማ ህፃኗን ሶፊያ ብላታለች። የአውሮፓ ኅብረት ሜዲቴራኒያን ላይ ፍልሰተኛ በድብቅ በማሻገር የሚጠረጠሩ ጀልባዎችን እያሳደደ ከሚይዝባቸው ስምሪቶቹ አንዱን “ዘመቻ ሶፊያ” ሲል ሰይሞታል።

“ልጄ ዕድለኛ ነች” ስትል ደስታዋን የምትገልፀው ራህማ የአውሮፓ ኅብረት “ለኔም ጥገኝነት፣ ለሶፊያም ዜግነት ይፈቅድልናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” ብላለች።

ልጄ ዕድለኛ ነች ለኔም ጥገኝነት፣ ለሶፊያም ዜግነት ይፈቅድልናል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ
ሶማሊያዊት ስደተኛ ራህማ አሊ

ራህማ ሌሎች ሰባት ልጆቿንና አባታቸውን ሶማሊያ ውስጥ ትታ አምስት ወር ሙሉ በአደገኛው መንገድ በስቃይ መጓዟን ትናገራለች፡፡

“… ልጆቼንና ባሌን ትቼ የተሻለ ኑሮና ተስፋ ፍለጋ የወጣሁት ጦርነቱና በጣም የከበደው ኑሮ አስገድደውኝ ነው …” ያለችው ራህማ ሌሎች ሰዎች ታዲያ በተለይ ነፍሰ ጡሮች ይህንን አደገኛ ጉዞ እንዳይሞክሩት ትመክራለች።

“በህገወጥ መንገድ መሰደድ በጣም ከባድ ነው። ሊብያ ውስጥ ብዙ ሶማሌዎችና ሌሎችም ፍልሰተኞች በህገወጥ አሻጋሪዎቹ የከበደ ጭካኔ ይፈፀምባቸዋል፤ ይሰቃያሉ። ህይወትህ በቋፍ ነው የምትሆነው። ለእርጉዝ ሴት ደግሞ ይብሱኑ ይከብዳል። መንገዱ ላይ መሞትም አለ” ብላለች ራህማ፡፡

የአውሮፓ ኅብረት የስደቱ ጎርፍ የሚገታበትን መንገድ መፈለጉን ቀጥሏል። በዚያ መሃልም አፍሪካዊያኑ ስደተኞች ህይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠው ወደዚያ መትመማቸውም አልቆመም።

ለተጨማሪ የተያያዙትን የድምፅና የቪድዮ ዘገባዎች ያዳምጡ፤ ይመልከቱ፡፡

የሜዲቴራኒያኑ ‘ዘመቻ ሶፍያ’ በልጇ የተሰየመው ሶማሊያዊት ታሪኳን ትናገራለች /ርዝመት -3ደ15ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:14 0:00

XS
SM
MD
LG