በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አባ ሙሴ ዘርአይ የኖቤል ሰላም ሽልማት እጩ


አባ ሙሴ ዘርአይ
አባ ሙሴ ዘርአይ

ለዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት ስዊዘርላንድ ነዋሪ የሆኑት ኤርትራዊው ቄስ አባ ሙሴ ዘርዓይ ታጭተዋል፡፡

ለዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት ስዊዘርላንድ ነዋሪ የሆኑት ኤርትራዊው ቄስ አባ ሙሴ ዘርዓይ ታጭተዋል፡፡ አባ ሙሴ በአውሮፓ ለስደተኞች ችግር እየተሟገቱ የሚገኙ ካቶሊክ ካሕን ናቸው፡፡

አርባ ዓመት ዕድሜአቸው ላይ የሚገኙት አባ ሙሴ በአፍሪካ፣ በአውሮፓ ውስጥና በሜዲቴራኒያን ባሕር ላይ እየታዩ ላሉ የስደትና የስደተኞች ችግሮች ለበርካታ ዓመታት ሲሟገቱ ቆይተዋል፡፡

ጣልያንና በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች ውስጥ የተበተኑ ስደተኞች ትኩረት እንዲያገኙ ለጣልያንና ለሌሎች የአውሮፓ ሃገሮች መንግሥታትና ባልሥልጣኖች አቤቱታዎችን ሲያቀርቡና ሲጎተጉቱ ቆይተዋል፡፡

የኖቤል ሰላም ሽልማት

​አባ ሙሴ የአውሮፓ መሪዎች ለችግሩ የሚገባውን ትኩረት አልሰጡም ብለው እስከ ዛሬ እየተሟገቱ ይገኛሉ፡፡

አባ ሙሴ ሜዲቴራኒያን ባሕር ላይ ለአደጋ ከተጋለጡ ፍልሰተኞች የሚደርሷቸውን የ“ድረሱልን” ጥሪዎች ለጣልያንና ለማልታ የባሕር ኃይሎች እያቀበሉ በባሕር ላይ የነፍስ አድን ሥራዎች እንዲጀመሩ ላለፉት 12 ዓመታት ሲጥሩ የኖሩ ሰው ናቸው፡፡

ያለ ፍትህ ያለ ነፃነት ያለ ዲሞክራሲ የሰው ልጅ መሰረታዊ መብቶች ሳይከበሩ ሰላም አይኖረንም
ቄስ አባ ሙሴ ዘርዓይ

አባ ሙሴ ባለፈው ዓመት አጋማሽ አካባቢ ከሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሣት አቡነ ፍራንሲስ ጋር ተገናኝተው በነበረ ጊዜ እያከናወኑ ስላሏቸው ለስደተኞች ደኅንነት የመሟገት ተግባራት ተነጋግረው ነበር፡፡

የሮማው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሣት አቡነ ፍራንሲስ እኤአ 2013 የአበባ ጉንጉን በሜዲቴራኒያን ባሕር ላይ ሲያኖሩ

አባ ሙሴ ለዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት ስለመታጨታቸው ምን እንደሚሉ፣ የዚህ ዛሬ ዛሬ እንዲህ በእጅጉ ተስፋፍቶ ለሚታየው የስደት ችግር መፍትሔው ምንድነው ብለው እንደሚያስቡና ስለስደተኞች መከራና ሰቆቃም ጳጳሱ የአባ ፍራንሲስ ስላሏቸው አስተሳሰብና ዕውቀትም አባ ሙሴ ገልጽዋል፡፡

የአባ ፍራንሲስ ለቫቲካን የበላይነት መመረጥ ማኅበራዊ ፍትሕን ያስገኛል ብለው እንደሚያምኑና ሌሎች ካሕናት በእርሣቸው ምክንያት ተመሣሣይ ተግባር ለመፈጽም እንደሚበረታታቱ ገልጸዋል።

አባ ሙሴ ለታጩበት 106ኛ ለሆነው ለዘንድሮው የኖቤል የሰላም ሽልማት አብረዋቸው ከታጩት መካከል የሮማው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፍራንሲዝ እና የጀርመን ቻንስለር አንጌላ መርከል ይገኙበታል፡፡

ሳሌም ሰለሞን አባ ሙሴን በስልክ አነጋግራ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅራለች፡፡ ሙሉውን ዝርዝር የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

አባ ሙሴ ዘርአይ የኖቤል ሰላም ሽልማት እጩ /ርዝመት - 6ደ17ሰ/
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:17 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG