በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ሕብረት እና የኢትዮጵያ ግንኙነት 40ኛ ኢዮቤልዩ


የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ወኪል ፈረደሪካ ሞግሪኒ (Federica Mogherini)ባለፈው ሳምንት ኢትዮጲያን ጎብኝተው ነበር። ጉብኝታቸው የአውሮፓ ሕብረትን እና የኢትዮጲያን ግንኙነት አርባኛ ኢዮቤልዩ አስመልክቶ ሲሆን፣ በአዲስ አበባ በሚገኘው የአፍሪቃ ሕብረት አዳራሽ ጉባኤ ላይ ሕብረቱ ከአፍሪቃ እና ከኢትዮፕጵያ ጋር ያለውን አሰራር ለማዳበር የሚችልበትን ሁኔታዎችን በማንሳት ሃሳባቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው ሳምንት የአውሮፓ ሕብረት ከፍተኛ ወኪል ፈረደሪካ ሞግሪኒ (Federica Mogherini) ወደ ኢትዮጲያ በመሄድ የአውሮፓ ሕብረት እና የኢትዮጲያን ግንኙነት 40ኛ ኢዮቤልዩ ለማክበር በአዲስ አበባ ተገኝተው ነበር። ፈረደሪካ ሞግሪኒ በጉብኝታቸው፣ ከጠቅላይ ሚኒስተር ኃይለማርያም ደሳለኝ፣ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስተር ቴዎድሮስ አድሃኖም እና ከአፍሪቃ ሕብረት ሊቀወንበር ዶ/ር ንኮሳንዛ ድላሚኒ ዙማ ጋር ተገናኝተው በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል።

የአውሮፓ ሕብረት ከአፍሪቃ ጋር ያለውን ግንኙነት በተከያዩ መስኮች ማዳበር እንደሚችል አስታውቀዋል። በተለይም በኢኮኖሚ፣ መዋእለ ንዋይ፣ የዓለምአቀፉ የአካባቢ ጥበቃና የአየር ንብረት ለውጥ እና ከአፍሪቃ ወደ አውሮፓ የሚያመሩ ፍልሰተኞችን በሚመለከት በንግግራቸው ላይ አንስተው ሃሳባቸውን ገልጸዋል። እነዚህን ጉዳዮች ሕብረቱ ከአፍሪቃ ጋር በመስራት ለማሻሻል እንደሚጥርም አስታውቀዋል። ሴቶችን በማስልጠና እና የስራ እድሎችን መፍጠርን በተመለከተ እንዲህ ይላሉ ሞግሪኒ።

“እንደ ወጣት አውሮፓዊ ይህ አዲስ ትውልድ በአፍሪቃ ላይ ያለው አስተያየት ካለፈው የቀኝ ግዛት ታሪክ ነጻ የሆነ መጪውን በተግባራዊና ኃላፊነት በሚሰማው መንገድ መመልከት የሚፈል ነው። የናንተ ወጣቶች ብርታታችሁ እንደሆኑ የኛም እንደዛ ናቸው። በተጨማሪም ሴቶቻችሁ ብርታታችሁ እንደሆኑ በአውሮፓ የሚገኙ ሴቶችም ብርታታችን ናቸው። ይህን ደግሞ የሴቶችን መብት በአፍሪቃ እድገት ማእከል እንዲገኝ ባደረጉት ዋና ጸሓፊ ዙማ ፊት ስናገር ትልቅ ኩራት ይሰማኛል” ብለዋል።

​ይህንን ለመደገፍ ሞግሪኒ ከጎበኙት ቦታ አንዱ፣ የራስ አደር ሴቶች ድርጅት(ራሴድ) ይባላል። ራሴድ የበጎ አድራጎት ድርጀት ሲሆን፣ በዝቅተኛ-ገቢ ያሉ ሴቶችን በኢኮኖሚ የማብቃት ስራ ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው። የድርጅቱ ዳይረክተር ጽጌ ሃይሌ ድረጅቱ ከተቋቋመ ጀምሮ እስካሁን ብዙ ሴቶችን ለመርዳት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

የድርጅቱ ዳይረክተር ጽጌ ሃይሌ ለየአውሮፓ ሕብረት እና የኢትዮጲያ ግንኙነት 40ኛ ኢዮቤልዩ ለማክበር በሂልተን ሆቴል የኮክቴል ግብዣ በተደረገበት አጋጣሚ እንደተገኙ ከገለጹ በኋላ፣ በተለያዩ ርእሶች ላይ ተወያይተው መግባባት ላይ እንደደረሱ ገልጸዋል። የፍልሰተኞች ጉዳይ ከርእሶቹ አንዱ መሆኑንም አስረድተዋል። የአውሮፓ ሕብረት ዝርዝር ስለጉባኤው በዌብሳይታቸው ላይ አቅርበዋል። ይህንን ፋይል በመጫን ይጎብኙ።

ሳሌም ሰለሞን የራስ አደር ሴቶች ድርጅት (ራሴድ) ዳይረክተር ጽጌ ሃይሌን አነጋግራ ያቀረበችውን ዝርዝር ከተያያዘው ይድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የአውሮፓ ሕብረት እና የኢትዮጲያ ግንኙነት 40ኛ ኢዮቤልዩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:36 0:00

​ንግግራቸው እንዳበቃ ሞግሪኒ በቦታው ተገኝተው ከነበሩት የዓለምአቀፉ ጋዜጠኞች ጋር ቃለ-ምልልስ አካሄደው ነበር።

"ኤርትራን በተመለከተ ሀገሪቱውስጥ በአንድ በኩል የሰብዓዊ መብቶች ሬኮርድ፥ በሌላ ወገን ደግሞ የሕዝቡን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል አስፈላጊ መሆናቸው አጠራጣሪ አይደለም" ብለው መልስ ሰጥተዋል ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ። ሞግሪኒ ኤርትራ የውስጥ ችግሮቿን እንድታሻሽልም ጥሪ አቅርበዋል።ሙሉውን ቃለ ምልልስ ከተያያዘው የቪድዮ ፋይል ይመልከቱ።

"ከሁሉ አስቀድሞ የኤርትራውያን ሰብዓዊ መብቶቻቸው ሊከበሩላቸው ይገባል" ፈደሪካ ሞግሪኒ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:16 0:00

ከዚህ በፊትም ኤርትራ ከአውሮፓ ሕብረት ጋር ግንኙነቷን ለማሻሻል ጥረት እያደረገች መሆንዋን ዘግበን ነበር።​

XS
SM
MD
LG