በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት ወዲህ በመጠኑና አስከፊነቱ ታይቶ የማይታወቀው ድርቅ፤ በአፋር ክልል በእንስሳትና በሰዎች ህይወት ላይ ያሳደረው ጫና ከባድ ነው። በድርቁ በተጠቁ ሌሎች አካባቢዎችም ወደ ሰማንያ ከመቶ የሚሆኑ የቤት እንስሳት መሞታቸውን ዓለም አቀፍ የእርዳታ ሰራተኞች አስታውቋል። በአፋር ኤሊዳርና ገዋኔ ወረዳዎች ከብቶች በግጦሽና ውኃ እጥረት ሞተዋል፤ የተረፉት ደግሞ ሰውነታቸው መንምኖና በበሽታ ተጠቅተው ይታያሉ።
ሰዎች ይህንን ቆሻሻ ውኃ ነው የሚጠጡት። ይሔ ደግሞ የኑሮ ሁኔታቸውን ከማወክም አልፎ የበሽታዎችም መንስኤ ነው። ምክኒያቱም እንስሶች ከዚሁ ውኃ ነው የሚጠጡት እዛውም ነው የሚጸዳዱት።በአፋር ክልል ለአለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) የሚሰሩት ፓትሪክ ኮርማዋ
እንስሳትና ሰዎች ከአንድ የደፈረሰ ኩሬ ውኃ ይጠጣሉ። ንጹህ የመጠጥ ውኃ እጥረት ከድርቁ ጋር በተያያዘ ከተከሰተው የምግብ እጥረት ጋር ተያይዞ የሰዎችን ጤንነት እየተፈታተነ ይገኛል።
በአፋር ክልል ለአለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) የሚሰሩት ፓትሪክ ኮርማዋ ሁኔታውን ያስረዳሉ። "ሰዎች ይህንን ቆሻሻ ውኃ ነው የሚጠጡት። ይሔ ደግሞ የኑሮ ሁኔታቸውን ከማወክም አልፎ የበሽታዎችም መንስኤ ነው። ምክኒያቱም እንስሶች ከዚሁ ውኃ ነው የሚጠጡት እዛውም ነው የሚጸዳዱት። የዓለም አቀፍ ህብረተሰብ ፋኦን እና ሌሎች ድርጅቶችን እንዲተባበረን ነው የምንጠይቀው። የሚጠጣ ውኃ አቅርቦት ለእርሻ፣ ለእንስሳትም ሆነ ለሰዎች ማሟላት ነው አላማው። አሁን ያለው ሁኔታ ለአደጋ የሚጥል ሁኔታ ነው።" ብለዋል።
ከከባቢ አየር ለውጥ ጋር በተያያዘ በተለያዩ የደቡብ አፍሪካና ደቡብ አሜሪካ ሃገር ድርቅ ያስከሰተው ኤል ኒኞ፤ በኢትዮጵያ የፈጠረው የምግብ እጥረትና ድርቅ ከሁሉም የከፋ መሆኑን የገለጸው የዓለም የምግብ እና የእርሻ ድርጅት ፋኦ (FAO) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስቸኳይ እርዳታ ለኢትዮጵያ ሕዝብ እንደሚያስፈልግ አስታውቋል።
የዓለም አቀፍ ኅብረተሰብ ፋኦን እና ሌሎች ድርጅቶችን እንዲተባበረን ነው የምንጠይቀው። የሚጠጣ ውኃ አቅርቦት ለእርሻ፣ ለእንስሳትም ሆነ ለሰዎች ማሟላት ነው አላማው። አሁን ያለው ሁኔታ ለአደጋ የሚጥል ሁኔታ ነው።በአፋር ክልል ለአለም የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) የሚሰሩት ፓትሪክ ኮርማዋ
በተለይ በአርብቶ አደር አካባቢዎች፤ እንደ አፋርና ሶማሊ ክልል እንዲሁም አንዳንድ የአማራና ኦሮሚያ ቆላማ አካባቢዎች በግጦሽና ውኃ እጥረት የተነሳ እንስሳቶች በመሞታቸው፤ የወተትና ስጋ ምርት ቀንሷል። በዚህም የተነሳ የአካባቢው ማኅበረሰብ ለከፋ የምግብ እትረት ተጋልጧል።
"ሃያ አምስት ፍየሎች ሞተውብኛል። ላሞችና በሬዎች ሙሉ በሙሉ ለማለት ይቻላል አልቀዋል። የእንስሳት መኖና ጭድ እርዳታ አግኝተን ጥቂት ከብቶች ተርፈውልናል። ሆኖም በቂ አይደለም። አሁንም ተጨማሪ የእንስሳት መኖ ያስፈልገናል። የቀሩት እንስሳት ከቀን እስኪደርሱ ቀለብ ያሻቸዋል።"ይላሉ ገበሬ ኦመር ቤሪ።
ለመጠጥና ለእንስሳት የሚውለው ውኃ በአቅራቢያ ካለ ወንዝ በሞተር ተስቦ ወደ ኩሪው ይገለበጣል። በወንዙ ዳርቻ ላሉ ሰዎች ቅርበት ቢኖረውም፤ በሌሎች አካባቢዎች ከዝናብ የሚገኝ ውኃ የሚቋርባቸው ኩሪዎችና ኢላዎች ደርቀዋል። በዚህም የተነሳ አርብቶ አደሮች ውኃ ለማግኘት ለሰዓታት ይጓዛሉ። በቋፍ ላይ ያሉ፣ የታመሙና የደከሙ እንስሳት ረጂም ርቀት ለመጓዝ ስለማይችሉ በመንገድ ወድቀው ይቀራሉ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው መረጃ መሰረት፣ በአህጉሪቱ ደቡባዊ ክልል በመላው አፍሪቃ ወደ 20 ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎች የምግብ እጥረት ተጠቅተዋል፣ ወደ 14 ሚልዮን የሚሆኑ ሰዎች ደግሞ በምስራቅ በሚገኘው አካባቢ በድርቁ እንደተጠቁ ገልጿል።
ኤል ኒኞ በአፍሪካ ያስከተለው ድርቅና ጎርፍ ሲሆን፤ ያልተመጣጠነና ወቅቱን ያልጠበቀ የዝናብ ዝርጭት በአንዳንድ ቦታዎች ሰብል ሲያደርቅና እንስሳትን ሲገድል፤ በሌሎች አካባቢዎች ደግሞ የጎርፍ መጥለቅለቅ ያስከትላል።
Your browser doesn’t support HTML5