በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ነውጠኞች በየመን ባደረሱት ጥቃት በትንሹ 15 ሰዎችን ገድለዋል


የየመን ካርታ
የየመን ካርታ

ጥቃት አድራሾቹ ዛሬ ጠዋት ወደ አዛውንቱ ማረፊያ ቤት የገቡት አውቶማቲክ የጦር መሣሪያ ተኩስ ከፍተው መሆኑን፥ የፀጥታ ባለሥልጣናቱ ጨምረው ገልጸዋል።

በየመን ባለሥልጣናት መግለጫ መሠረት፥ አንድ የጡረተኞች መኖሪያ ቤት ሠብረው የገቡ ነውጠኞች፥ አራት የክርስትና እምነት ተከታይ የሆኑ የሕንድ መነኮሳትን ጨምሮ በትንሹ 15 ሰዎችን ገድለዋል።

ጥቃት አድራሾቹ ዛሬ ጠዋት ወደ አዛውንቱ ማረፊያ ቤት የገቡት አውቶማቲክ የጦር መሣሪያ ተኩስ ከፍተው መሆኑን፥ የፀጥታ ባለሥልጣናቱ ጨምረው ገልጸዋል።

ኤደን ከተማ ውስጥ በሚገኘው ”ድንበር የለሽ ሃኪሞች ሆስፒታል” የሚያገለግሉ ሠራተኞችና የአካባቢው ባለሥልጣናት ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት፥ ከተገደሉት መካከል አራቱ ሕንዳውያን መነኮሳት፥ ሁለት የሆስፒታሉ ሴት ሠራተኞች፥ ስምንት አዛውንትና አንድ ዘብ ይገኙበታል።

ለጥቃቱ እስካሁን ኃላፊነት የወሰደ የለም፥ ሆኖም እስላማዊ መንግሥት ነኝ የሚለው ጽንፈኛ ቡድን ከዚህ ቀደም ኤደን ውስጥ በተከታታይ ከደረሱ የሽብር ጥቃቶች ጋር ግንኙነት እንዳለው ተጠቅሷል። ደቡባዊው የወደብ ከተማ። ዓለምአቀፍ ዕውቅና የተሰጠውን የየመን መንግሥት በሚደግፈው በሳዑዲ አረቢያ በሚመራው የኅብረት ጦር ባለፈው ዓመት እንደገና በቁጥጥር ሥር መዋሉ ይታወቃል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮም፥ ምንም እንኳ በርካታ ሥርዓት አልባ እንቅስቃሴዎችና ውጊያ እየተካሄደ ቢሆንም፥ ኤደን የሃገሪቱ ጊዜአዊ ዋና ከተማ እንድትሆን ተወስኗል።

የታበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ኃላፊ በትላንትናው እለት፥ የመን ውስጥ በሲቪሎች ላይ ለሚካሄዱ ጥቃቶችሁሉንም ወገኖች ማውገዛቸው አይዘነጋም።

XS
SM
MD
LG