በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የየመን ሰላም ድርድር ተቋረጠ


በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሸምጋይነት ለስድስት ቀናት የተካሄደዉ የየመን ሰላም ድርድር በተደጋጋሚ ተኩስ አቁም ጥሰት ምክንያት ተቋረጠ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ልዩ መልክተኛ ኦሉድ ሼክ አህመድ (Ould Cheikh Ahmed) ድርድሩ የተቋረጠዉ በተደጋጋሚ በተከሰተዉ የተኩስ አቁም ጥሰት ምክንያት መሆኑን ገልጸዋል።

ድርድሩ ይካሄድ በነበረበት ወቅት የሳኡዲ አረቢያ የዓዬር ድብደባና የሁቲ ሸማዢዎች ዉጊያ እንዳልቆመ፣ ባለፉት ሶስት ሳምንታት ዉስጥ 75 ሰዎች እንደተገደሉም ተጠቁሟል።

የሰላም ድርድሩ ቢቋረጥም የመንግስት ደጋፊ ሃይሎችና የሁቲ ሽማቂዎች ልኡካን መተማመንን የሚያጠነክሩ አንዳንድ ነጥቦች ላይ እንደተስማሙ ተናግረዋል።

እንርሱም የእስረኞችን ሁሉ መፈታት ፣ ግጭት ወደሚካሄድባቸዉ ቦታዎች በተለይም ከፍተኛ ዉጊያ በሚካሄድባት የታይዝ (Taiz ከተማ) የስብአዊ እርዳታዎት በሰላምና በፍጥነት ስለሚደርሱበት ሁኔታ ላይ እንደተስማሙ ገልጸዋል። የመንግስታቱ ድርጅት ልዩ ተወካይ ድርድሩ በጥር ወር እንደገና እንደሚጀመር ተናግረዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

የየመን ሰላም ድርድር ተቋረጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:58 0:00

XS
SM
MD
LG