ዋሺንግተን ዲሲ —
የመን ውስጥ የተቀሰቀሰው የርስ በርስ ጦርነት በሳዑዲ አረቢያ የአየር ጥቃት ከተባባሰ ወዲህ ወደ የመን የሚገቡ ኢትዮጵያዊያንና ሌሎችም ፍልሰተኞች ቁጥር ማሽቆልቆሉን ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት - አይኦኤም አስታውቋል።
በመጋቢት አጋማሽ የሳዑዲ ዓረቢያ አየር ሃይል በየመን የሚደገፉት የኹጢ አማፂያን ይዞታዎችን በቦምብ መደብደብ ከመጀመሩ በፊት ባሉት ሁለት ሣምንታት ወደ የመን ይጎርፉ የነበሩ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞች ቁጥር በእጅጉ ጨምሮ እንደነበር አይኦኤም ገልጿል።
በደቡባዊቱ ግዙፍ ከተማ አደን በአየር ድብደባውና በተኩስ ልውውጡ መሃል ተጠምደናል የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችና ፍልሰተኛ ሠራተኞች በሚያሰሙት ተማፅኖ እንደቀጠሉ ነው፡፡
ለዝርዝሩ ዘገባዎቹን የያዘውን የተያያውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡