በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ የመን ከሚሰደዱት ዘጠና በመቶዉ ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ ተባለ

ፋይል ፎቶ - ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በምዕራብ የመን ከተማ ሃራዳ (Haradh) ውስጥ ወደ ሌላ ሃገር ለመጓዝ እየጠበቁ እአአ 2012 (ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)
ፋይል ፎቶ - ኢትዮጵያውያን ፍልሰተኞች በምዕራብ የመን ከተማ ሃራዳ (Haradh) ውስጥ ወደ ሌላ ሃገር ለመጓዝ እየጠበቁ እአአ 2012 (ፎቶ አሶሽየትድ ፕረስ/AP Photo)

የመን በግጭት እየታመሰች ቢሆንም የአፍሪቃ ቀንድ ሰደተኞች አሁንም ይጎርፉባታል ሲል የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) አስጠነቀቀ።

የመን በግጭት እየታመሰች ቢሆንም የአፍሪቃ ቀንድ ሰደተኞች አሁንም ይጎርፉባታል ሲል የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) አስጠነቀቀ።

Text: የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ባለፈዉ የአዉሮፓዉያን ዓመት በ2015 ወደ የመን ከገቡት 92, 446 ስደተኞች አብዛኞቹ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ዜጎች ናቸዉ ብሏል። ከእነዚሁ ስደተኞች ባለፈዉ ዓመት 95 ሰዎች እንደሞቱ ድርጅቱ ገልጾ፥ እንደ አዉሮፓዉያን አቆጣጠር በጥር 8፣ 36 ሰደተኞች በየመን ጉዞ ባህር ላይ እንደሞቱ ገልጿል።

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ድርጅት (UNHCR) እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር ከ2006 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ወደ የመን የሚሰደዱትን ሰዎች ቁጥርና መነሻ ሲዘግብ እንደነበር ጠቅሶ ፥ 2015 የመን ከገቡት ስደተኞች 90% ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ ብሏል። የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን የድምጽ ፋይል ያድምጡ።

ወደ የመን ከሚሰደዱት ዘጠና በመቶዉ ኢትዮጵያዉያን ናቸዉ ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:56 0:00

XS
SM
MD
LG