በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁጢዎች አደንን ያዙ


በሳዑዲ አረቢያ የአየር ድብደባ ዋና ከተማይቱ ሰንዓ ውስጥ የፈረሰ ሕንፃ
በሳዑዲ አረቢያ የአየር ድብደባ ዋና ከተማይቱ ሰንዓ ውስጥ የፈረሰ ሕንፃ

የመን ውስጥ እየተፋለሙ ያሉት ሺአ ሁጢ አማፂያን እና ረዳቶቻቸው ሁለተኛይቱ ግዙፍ ከተማ አደን ውስጥ ገብተው የፕሬዚዳንቱን ቤተመንግሥት ያዙ፡፡

ሰንዓ-የመን፤ የፕሬዚዳንቱ ቤተመንግሥት አጠገብ - መጋቢት 24/2007 ዓ.ም
ሰንዓ-የመን፤ የፕሬዚዳንቱ ቤተመንግሥት አጠገብ - መጋቢት 24/2007 ዓ.ም

የመን ውስጥ እየተፋለሙ ያሉት ሺአ ሁጢ አማፂያን እና ረዳቶቻቸው ሁለተኛይቱ ግዙፍ ከተማ አደን ውስጥ ገብተው የፕሬዚዳንቱን ቤተመንግሥት ያዙ፡፡

ባለፉ ጥቂት ቀናት ውስጥ አማፂያኑ በሳዑዲ አረቢያ ከሚመሩትና ዓለምአቀፍ ዕውቅና ያላቸው ፕሬዚዳንት አብድ-ራቡ መንሱር ሃዲ ደጋፊዎች ከሆኑ ኃይሎች ጋር እየተዋጉ ወደዚህች ደቡባዊት የወደብ ከተማ ሰሞኑንም ዘልቀው ሲገሠግሡና ዛሬም ወደ ከተማይቱ ማዕከል ሲገፉ እንደነበር ተዘግቧል፡፡

የአደን መውደቅ ከአንድ ሣምንት በላይ ለሆነ ጊዜ በመላ የመን የአየር ድብደባ እያደረሰ ባለው በሣዑዲ አረቢያ የሚመራው ጥምር ኃይል ላይ ያረፈ ከባድ የክርን ጥቃት ነው እየተባለ ነው፡፡

ሳዑዲ አረቢያ ዋና ከተማ ሪያድ ላይ መግለጫ የሰጡ አንድ የሳዑዲ መከላከያ ባለሥልጣን ከተማይቱ ውስጥ ያለው ሁኔታ የተረጋጋ ነው ብለው እንደሚያምኑ አመልክተዋል፡፡

Al-Mukalla, Yemen
Al-Mukalla, Yemen

በሌላ በኩል ደግሞ ከአል-ቃዳይ ቁርኝት ያላቸው ናቸው የተባሉ ታጣቂዎች ደቡብ የመን ውስጥ የሚገኝ አንድ እሥር ቤት ወርረው 300 የሚሆኑ እሥረኞችን ማስለቀቃቸው ተገልጿል፡፡

አል-ማካላ በሚባለው አባባቢ ከሚገኘው እሥር ቤት ዛሬ እንዲያመልጡ ከተደረጉት መካከል የአል-ቃይዳ በአረቢያ ልሣነ-ምድር መሪ የሆነ ኻሊድ ባታርፊ የሚባል ሰው እንደሚገኝበት የፀጥታ ባለሥልጣናት ተናግረዋል፡፡

በሌላ ዜና ደግሞ አንድ የሳዑዲ አረቢያ የወሰን ጥበቃ ጓድ አባል ዛሬ መገደሉን የሳዑዲ አረቢያ ዜና ወኪል ዘግቧል፡፡

ወታደሩ የተገደለው ከየመን ግዛት በተተኮሰ ጥይት መሆኑም ተገልጿል፡፡

የዚህ ወታደር መገደል ሳዑዲ አረቢያ በሁጢዎቹ አማፂያን ላይ ጥቃት ከከፈተች ወዲህ ባለው የአንድ ሣምንት ጊዜ ውስጥ የመጀመሪያው በሕይወት ላይ የደረሰባት ጉዳት መሆኑ ነው፡፡

XS
SM
MD
LG