በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በየመን ኢትዮጵዊያን ድንበር ተሻጋሪ ሥራ ፈላጊዎች ላይ የሚፈጸሙ በደሎች

የሳዑዲ-የመን ድንበር አጥር
የሳዑዲ-የመን ድንበር አጥር

ጦርነት ባነተባት የመን በድንበር ተሻጋሪ ሥራ ፈላጊዎች ላይ ከሚፈፀሙ በደሎች መካከል የተንሠራፋ አስገድዶ ገንዘብ መዝረፍ እንደሚገኝበት ዓለምአቀፉ የፍልሰት ጉዳዮች ድርጅት - አይኦኤም ይናገራል፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:02:45 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ጦርነት ባነተባት የመን በድንበር ተሻጋሪ ሥራ ፈላጊዎች ላይ ከሚፈፀሙ በደሎች መካከል የተንሠራፋ አስገድዶ ገንዘብ መዝረፍ እንደሚገኝበት ዓለምአቀፉ የፍልሰት ጉዳዮች ድርጅት - አይኦኤም ይናገራል፡፡

አይኦኤም እንደሚለ ሕገ-ወጥ አስተላላፊዎች፣ የታጠቁ ቡድኖችና ሌሎች ወደ ሳዑዲ አረቢያ የሚፈልሱ መከታ የሌላቸውን ኢትዮጵያውያን በማገት ለማስለቀቂያ ገንዘብ እያስከፈሉ ነው።

ዓለምአቀፉ የፍልሰት ድርጅት የመን ውስጥ እየተካሄደ ባለው የርስ በርስ ጦርነት ምክንያት መግቢያ ያጡ 3500 ኢትዮጵያውያንን ወደ አገር በመመለስ ረድቷል።

ከተመላሾቹ ጋር በተደረገ ሰፋ ያለ ቃለ ምልልስ ሕገ-ወጥ ድንበር አሸጋጋሪዎች አንዳንዶቹን እያገቱ የማስለቀቂያ ገንዘብ እንደሚያስከፍሉ እንደሚደበድቡና የሥቃይ ድርጊት እንደሚፈፅሙባቸው ተመልክቷል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG