ዋሺንግተን ዲሲ —
በየመን በሺአ ሁጢ አማፂያንና በሀገሪቱ ፕሬዚደንት ታማኝ ኃይሎች መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው።
በሳዑዲ አረቢያ የሚመራው ኅብረት ጄቶች በሺአ ሁጢ ሸማቂዎቹ ይዞታዎች ላይ ላለፉት ሁለት ሣምንታት ድብደባ ሲያካሂዱ ቆይተዋል።
በዚያች ድሃ ሃገር ያለው ሁኔታ እጅግ በጣም ኣሳሳቢ መሆኑን የእርዳታ ድርጅቶች ሲያስገነዝቡ ቆይተዋል።
የመን ውስጥ በሺሆች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እንዲሁም የሥራ ፍልሰተኞች አሉ።
“ከተማይቱ በአሥሮፕላን እየተደበበደበች ነው፤ ካለንበት እየሸሸን ነው፤ የሽሽት ነገር ሆኖ ነው እንጂ እዚህ ቦታ ብንሄድ እንተርፋለን ብለን አይደለም፤ ወዳገኘነው አቅጣጫ ነው የምንሄደው፤ ወደ ሦስት መቶ እንሆናለን” ብለዋል።
ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።