አዲስ አበባ —
የአፍሪካ ኅብረት የያዝነውን የአውሮፓ 2016 ዓ.ም “የአፍሪካ የሰብዓዊ መብቶች ዓመት” ብሎ ሰይሞታል።
ከዚህ አንፃር በአዲስ አበባ ላይ የተካሄደው የኅብረቱ የመሪዎች ሃያ ስድስተኛ ጉባዔ የሚያሣልፋቸው ውሣኔዎችና ደንቦች በአባል ሃገሮች የማይከበሩበት ሁኔታ መኖሩ ፈታኝ መሆኑን አስታውቋል።
በጉባዔው ላይ የሚሣተፉ የሃገሮች መሪዎች በአዲስ አበባ ይገኛሉ። ዩናይትድ ስቴትስም በዚሁ የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ላይ ተገኝታለች። የዩናትድ ስቴትስ ልዑካን ቡድን የሚመራው በዓለም አቀፉ የልማት ኤጀንሲዋ - ዩኤስኤአይዲ ዋና አስተዳዳሪ መሆኑንም ታውቋል።
እስክንድር ፍሬው አርብ ከአዲስ አበባ የላከውን ዘገባ ከዚህ በታች ካለው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።