በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በየመኑ ውጊያ ሕጻናት ለእልቂት እየተዳረጉ ነው ሲል ዩኒሴፍ አስጠነቀቀ


“ቁጥራቸው 10 ሺህ የሚጠጋ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ሕጻናት ጨርሶ በተንኮታኮተው የአገሪቱ የጤና አገልግሎት ሳቢያ ሊታከሙ በሚችሉ በሽታዎች እንዳያልቁ ከፍተኛ ሥጋት አለኝ።” በየመን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሕጻናት መርጃ ፕሮግራም ዩኒሴፍ (UNICEF)ተጠሪ ጁልየን ሃርኒስ

በየመን እየተካሄደ ካለውና አንድ ዓመት ከሞላው እጅግ የከፋ ውጊያ ጋር በቀጥታና በተዘዋዋሪና በተያያዙ ችግሮች ሳቢያ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ሕጻናት እያለቁ ናቸው፤ ሲል አንድ አዲስ ዘገባ አመለከቱ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሕጻናት መርጃ ተቋም እንዳመለከተው፤ ሰብዓዊ ሁኔታው በፍጥነት እያሽቆለቆለ ነው። የመን ቀድሞውንም ለዓመታት ከራሷ ጋር ጦርነት የገጠመች አገር ነበረች።

ሳውዲ አረቢያ በዚያ የሚካሄደውን ጦርነት ከተቀላቀለችበት አንድ ዓመት አንስቶ ግን፤ የውጊያው መጠንና እያስከተለ ያለው ጉዳት ከዚህ ቀደም ያች አገር አይታ ከማታውቀው እጅግ የከፋ ደረጃ ደርሷል።

የየመኑን ውጊያ ተከትለው የሚመጡ ሌሎች ውስብስብ ችግሮችን መከላከል ካልተቻለ የጉዳት መጠኑ በቀላሉ የማይገመትና ሥር የሰደደ ጣጣ ይከተላል፤ ሲሉ የዩኒሴፉ ባለሥልጣን አስጠንቅቀዋል።

በየመኑ ውጊያ ሕጻናት ለእልቂት እየተዳረጉ ነው ሲል ዩኒሴፍ አስጠነቀቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:20 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG