በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኡጋንዳ መንግሥት ተቃዋሚውን ፓርቲ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ፈቃዳቸውን ይነጠቃሉ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጠ


የኡጋንዳ መንግሥት በሰጠው ማስጠንቀቂያ፣ የተቃዋሚውን ኤፍ ዲ ሲ ፓርቲ (FDC Party) እንቅስቃሴ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ፈቃዳቸውን ይነጠቃሉ፣ ሊታሰሩም ይችላሉ ብሏል። ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ ለ5ኛ ጊዜ አሸናፊ የሆኑበት እ.አ.አ. የየካቲት 18ቱ ፕሬዚደንታዊ ምልጫ ከተካሄደ ወዲህ፣ ኡጋንዳ ውስጥ ውጥረት እንደሰፈነ ነው።

የኡጋንዳ መንግሥት በሰጠው ማስጠንቀቂያ፣ የተቃዋሚውን ኤፍ ዲ ሲ ፓርቲ (FDC Party) እንቅስቃሴ የሚዘግቡ ጋዜተኞች ፈቃዳቸውን ይነጠቃሉ፣ ሊታሰሩም ይችላሉ ብሏል።

ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ /ፋይል ፎቶ/
ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ /ፋይል ፎቶ/

ፕሬዚደንት ዮዌሪ ሙሴቪኒ ለ5ኛ ጊዜ አሸናፊ የሆኑበት እአአ የየካቲት 18ቱ ፕሬዚደንታዊ ምልጫ ከተካሄደ ወዲህ፣ ኡጋንዳ ውስጥ ውጥረት እንደሰፈነ ነው።

የዛሬው ሐሙስ፣ "ባለፈው ፕሬዚደንታዊ ምርጫ የተመዘገበው ድምፅ በነፃ አካል ይመርመርልን" የሚል ጥያቄ ያነሱ የተቃዋሚው FDC ባለሥልጣናትና ደጋፊዎቹ፣ ሰላማዊ ሰልፍ የሚያደርጉበት ቀን ነበር።

ይሁንና መንገዶች በፖሊስ ታጥረዋል፤ እጩ ፕሬዚደንታዊ ተወዳዳሪ ሆነው የቀረቡት የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ ኪዛ ቤሲጄም በቁም እስር ውለዋል። ዋናው የፖሊስ ተቆጣጣሪና የማስታወቂያ ሚኒስትሩ ዛሬ ሐሙስ በጠሩት ጋዜታዊ ጉባዔ፣ መንግሥት "አፍራሽ" ያለውን ይህን የተቃዋሚው ፓርቲ በምርጫው ዙሪያ የሚያሰራጨውን እንቅስቃሴ መገናኛ ብዙኃን ዘገባ እንዳያቀርቡና ምንም ዓይነት ሽፋን እንዳይሰጡ ከልክለዋል።

የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ ኪዛ ቤሲጄ /ፋይል ፎቶ/
የተቃዋሚው ፓርቲ መሪ ኪዛ ቤሲጄ /ፋይል ፎቶ/

ሮበርት ስሴምፓላ ኡጋንዳ ውስጥ የሚገኘው የጋዜጠኞች ሰብዓዊ መብት ጥበቃ መረብ ዋና አስተባባሪ ናቸው። "ይህ አሳሳቢ ትዕዛዝ ነው" ይላሉ። "ዘገባዎችን ሚዛናዊ አድርጎ በማቅረብ፣ ሥልጣን ላይ ላሉትም ሆነ ከዚያ ውጪ የተለየ ሃሳብ ላላቸውም ተገቢውን ሽፋን በመስጠት እረገድ ሙያው በጣም ግልጥ ነው። የመገናኛ ብዙኃን ሥራም ይኸው ነው። እና አሁን የመገናኛ ብዙኃኑ ከዚያ ወጥቶ የመንግሥት ልሳን እንዲሆን ነው የምትፈልጉት? ይሄማ ጋዜተኛነት አይደለም።" ብለዋል።

መንግሥት፣ "የአገሪቱን ሰላምና መረጋጋት ማስጠበቅ አለብኝ" ባይ ነው። የመብት ተሟጋቾች የሚቃወሙት ደግሞ፣ መገናኛ ብዙኃኑ በፍርድ ቤት የተጣለባቸውን እገዳ ነው" ብለዋል ስሴምፓላ። "ይህ እገዳ ሳይጣልባቸው ገና፣ ጋዜጠኞች እየታሰሩ ናቸው" ያሉት ስሴምፓላ፤ "አቅጣጫውም ወደፊት ሌላ እገዳ፣ እስርና እንግልት እንደሚደርስባቸው ጠቛሚ ነው" ሲሉ አመልክተዋል።

የማህበራዊ ሚዲያዎች፣ ባለፈው በየካቲቱ ምርጫ ጊዜ እንደተዘጉት፣ ዛሬ አልተዙም። አንድ የኡጋንዳ የኰሚኒኬሽንስ ኮሚሽን ባለሥልጣን እንዳስታወቁት ግን፣ ባይዘጉም፣ ስለ ተቃዋሚዎች ፓርቲ የሚያቀርቡት ዘገባ በሙሉ፣ ቁጥጥር ይደረግበታል።

ሊዛቤት ፑላንት ከካምፓላ የላከችው ዘገባ አለ፣ አዲሱ አበበ አቅርቦላል። ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

የኡጋንዳ መንግሥት ተቃዋሚውን ፓርቲ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ፈቃዳቸውን ይነጠቃሉ የሚል ማስጠንቀቂያ ሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:33 0:00

XS
SM
MD
LG