በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኡጋንዳ ተቃዋሚ ድርጅት በተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ የሚወሰደው የመጪውን ብሄራዊ ምርጫ ለማሰናከል ነው ይላሉ


የኡጋንዳ ተቃዋሚ መሪዎች በካምፓላ[ፋይል ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ/AP]
የኡጋንዳ ተቃዋሚ መሪዎች በካምፓላ[ፋይል ፎቶ - አሶሽየትድ ፕረስ/AP]

ዋናው የኡጋንዳ ተቃዋሚ ድርጅት ፖሊሶች በተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ የሚወስዱት በመጪው የካቲት ወር የሚካሄደውን ብሄራዊ ምርጫ ለማሰናከልና ፕረዚዳንት ዮዌሪ ሙሴቬኒ በስልጣን ላይ እንዲቆዩ ለማመቻቸት ነው ብለዋል።

የኡጋንዳ ፖሊሶች ትላንት በሀገሪቱ ምስራቅ ክፍል ቡኩዎ በተባለው ወረዳ ላይ ለፕረዚዳንትነት የሚወዳደሩት ዋናው የተቃውሚዎች መሪ ኪዛ በሲጄ (Kizza Besigye) ደጋፊዎችን ለመበተን እምባ አስመጪ ጋዝና የጎማ ጥይት ተኩሰዋል።

የሀገሪቱ ፖሊስ ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ትላንት ለተከሰተው ግጭት ተጠያቂዎቹ የተቃዋሚዎች መሪ ኪዛ በሲጄ (Kizza Besigye) እና ደጋፊዎቹ ናቸው ብለዋል። በግጭቱ አንድ ፖሊስና ሁለት ሌሎች ሰዎች ቆስለዋል።

ባለስልጣኖች እንደሚሉት ችግር የተፈጠረው የተቃዋሚዎቹ መሪና ደጋፊዎቻቸው በተደጋጋሚ ማስጠንቀቅያ ቢሰጣቸውም ተፈናቃዮች ወደ ሚገኙበት ሰፈር የፖሊስ ከበባን ሰብረው በገቡበት ወቅት ነው።

በሲጄ (Kizza Besigye) በበኩላቸው የምርጫ ዘመቻ ላይ በመሆናችን ሁለት የምርጫ ዘመቻዎች በአንድ ቦታ ላይ እስካልተካሄዱ ድረስ ደጋፊዎቻችን ባሉባት ቦታ ሁሉ መደረስ አለብን ይላሉ።

“የምርጫ ዘመቻ ላይ በመሆናችን ደጋፊዎቻችን ባሉባት ቦታ ሁሉ የቻልነውን ያህል መደረስ አለብን። ሚድያም ሆና ሃዝባዊ ስብሰባዎችን መጠቀም አለብን። ጥንቃቄ ማድረግ የሚያስፈልገው ዘመቻ በሚያካሄዱት ወገኖች መካከል ግጭት እንዳይነሳና ሁለት የተላያዩ ዘመቻዎች በአንድ ቦታ ላይ እንዳያደርጉ ነው። ብሄራዊው የምርጫው ኮሚሽን እንደሆነ የፕረዚዳንት ሙሴቬኒ አፈ-ቀላጤ ነው" ብለዋል።

የፖሊስ ኮሚሽነርም ጭምር የሆኑት የፖሊስ ጽህፈት ቤት ቃል አቀባይ ፍሬድ ኢናንጋ ግን የተቃዋሚዎቹ መሪና ደጋፊዎቻቸው የምርጫ ዘመቻ ከመጀመሩ በፊት ስምምነት የተደረገባቸውን መስመሮች ጥሰዋል ይላሉ።

የኡጋንዳ የአገር ውስጥ አስተዳደር ሚኒስትር ጀምስ ባባ ፖሊሶች በተቃዋሚዎቹ ላይ የወሰዱት እርምጃ በሀገሪቱ ህገ-መንግስት መሰረት የፖሊሶችን ሚና በመከተል ነው ሲሉ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል።

የእግሊዘኛ ክፍል ባልደረባችን ጀምስ ባቲ ያጠናቀረውን ዘገባ አዳነች ፍሰሀየ አቅርባዋለች።

የኡጋንዳ ተቃዋሚ ድርጅት በተቃዋሚዎች ላይ እርምጃ የሚወሰደው የመጪውን ብሄራዊ ምርጫ ለማሰናከል ነው ይላሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:31 0:00

XS
SM
MD
LG