በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዑጋንዳ ለፕረዚዳንትነት የተወዳደሩት ተቃዋሚዋች እስራትና ወከባ እንደደረሰባቸው ገለጹ


የቀድሞ የኡጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አማማ እመባባዚ (Amama Mbabazi) - ፋይል ፎቶ
የቀድሞ የኡጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አማማ እመባባዚ (Amama Mbabazi) - ፋይል ፎቶ

በዑጋንዳ ለፕረዚዳንትነት የሚወዳደሩት የቀድሞ የኡጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር አማማ እመባባዚ (Amama Mbabazi) ባለፈው ሃሙስ ምርጫ ከተደረገ በኋላ መኖርያ ቤታቸው ለጥቂት ቀናት ያህል በሀገሪቱ ወታደራዊና መደበኛ ፖሊሶች ተከቦ ነበር ብለዋል። ምርጫው መሰረታዊ የሆኑ ጉድለቶች ነበሩበት። ይፋ የተደረገው ውጤትም የህዝቡን ፍላጎት አያንጸባርም ሲሉ አማማ እመባባዚ ተናግረውል።

አማማ እመባባዚ (Amama Mbabazi) መኖርያ ቤታቸው በተከበበት ወቅት ወደ ቤታቸው የሚሄዱ ስዎች እንደታሰሩ ገልጽዋል። የቤት ሰራተኛቸው ሳትቀር ተይዛ ለሁለት ቀናት ያህል ጠፍታ ነበር ብለዋል። በቀጥታ ከመንግስት የተነገራቸው ነገር ባይኖርም በድርጅታቸው ላይም ገደብ እንደተጣለ ለአከባቢው ሚድይ አሳውቀዋል።

መንግስት በምርጫው ወቅት የተወዳዳሪዎችን የመዘዋወር መብት ለመንፈግ የመንግስትን መሳርያ ተጠቅሟል ሲሉ አውግዘዋል።

ምርጫው መሰረታዊ የሆኑ ጉድለቶች ነበሩበት። ይፋ የተደረገው ውጤትም የህዝቡን ፍላጎት አያንጸባርም ብለዋል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር።

“መግለጫ አውጥቼ ነበር። የምርጫ ዘመቻ ውስጥ ከገባሁበት ጊዜ አንስቶ የምርጫው ሂደት እኩል አልነበረም የሚል መግለጫ። እንደምታውቁት መንግስት እኔን በግል ለማዋከብ የተቻለውን ሁሉ የመንግስት አካላትን ተጠቅሟል። አስረውኛል ሰነዶቼንም ወስደዋል። የመንግስት የሆነውን የስርጭት ዘዴ እንዳልጠቀም እድል ነፍገውኛል።”ብለዋል።

የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን በግልጽ በስልጣን ላይ ላሉት ፕረዚዳንት የሚያዳላ ወገንተኛ ነው።

ይፋ የተደረገው ውጤትም በብዙ መንገድ የተጭበረበረ ነው ብለዋል የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር።

ቡድናቸወ በምርጫው ወቅት ስተለፈጸሙት ነገሮች ሁሉ መረጃ ሰብስቦ ካጠናቀቀ በኋላ ስለ ሚወስዱት እርምጃ እንደሚወስኑ ጠቁመዋል።

ቡድናቸው ካሰባቸው እርምጃዎች መካከል የምርጫውን ውጤት በመቃወም ለፍርድ ማቅረብና የፖለቲካ ጫና ማደርግ እንደሚገኙባቸው አማማ እመባባዚ ጨምረው ገልጸዋል።

ዋናው የተቃዋሚዎች መሪ ተወዳዳሪ ዶክተር ኪዛ በሲጅየም በቁም እስር ላይ ውለዋል። ማንም ቤቴ ሊደርስ አይችልም። በመኖርይ ቤቴ ማንኛውንም አይነት የኢንተርነት አገልግሎት ለማግኘት አልቻልኩም ማለታቸው ተዘግቧል።

የፕረዚዳንት ኦባማ አስተዳደር የበሰጅየ በቁም እስርነት መቀጠል እዳሳሰበው ኡጋንዳ ያለው የዩናይትስድ ስቴስ ኤምባሲ አስታውቋል። “በአስቸውኳ ተፈተው ለሁሉም ማህበረሰባዊ ሚድያ ተደራሽነት እንዲመለስላቸው ጥሪ እናቀርባለን” ሲሉ ቃል አቀባይ ክሪስቶፈር ጄ ብራውን በመግለጫ ጠቅሰዋል።

የእንግሊዘኛው ክፍል ባልደረባችን ጀምስ ባቲ ያጠናቀረውን ዘገባ አዳንች ፍስሀየ ታቀርበዋለች።

በዑጋንዳ ለፕረዚዳንትነት የተወዳደሩት ተቃዋሚዋች እስራትና ወከባ እንደደረሰባቸው ገለጹ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:18 0:00

XS
SM
MD
LG