የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት 71ኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጎን በስደተኞች ጉዳይ ላይ የመሪዎች ጉባዔ እ.አ.አ. በመጪው መስከረም ወር ያስተናግዳሉ።
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የዩናይትድ ስቴትስ አምባሳደር ሳማንታ ፓወር ከቋሚ የድርጅቱ ተወካዮች እንዲሁም ስብሰባውን አብረው ከሚያስተናግዱት ካናዳ፣ ኢትዮጵያ፣ ጀርመን፣ ዮርዳኖስ፣ ስዊድን ተወካዮችና ከመንግሥታቱ ድርጅት ዋና ጸሀፊ ባን ኪ ሙን ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል ሲሉ የብሄራዊ ጸጥታ አማካሪ ሱዛን ራይስ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል።
ጉባዔውን የሚያስተናግዱት መሪዎች የጉባዔውን አላማ ለማራመድ በቅርብ ተባብረው ለመስራት ቃል እንደገቡም ጠቁመዋል።
በአለም ደረጃ 20 ሚልዮን የሚሆኑ ሰደተኞች ስላሉ ሰደተኞቹን የመርዳትና ደህንነታቸዋን የመጠበቁ ተግባር አለም አቀፍ ጥረት ያስፈልገዋል። ጉባኤውን የሚመሩት ሁሉም አለመ አቀፍ ማኅበረሰብ ሰደተኞቹን ለመርዳትና ለመጠበቅ የበለጠ መስራት እንደሚያስፈልግ ይገነዘባሉ ሱሉም ሱዛን ራይስ አውስተዋል።
ከፍተኛ ብዛት ያላቸው ስደተኞች አደገኛና ህገ-ወጥ የሆነ ዘዴ እየተጠቅሙ እንደሆኑ በገቡባቸው ሀገሮችም ለህጋዊ የስራና የትምህርት እድል ተደራሽነት እንደማያጘኑ ሱዛን ራይ ባወጡት መግለጫ ጠቅሰዋል።