ዋሽንግተን ዲሲ —
ዋኡ በተባለችው የደቡብ ሱዳን ከተማ የሚገኙ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኤርትራውያን የንግድ መደብሮች፣ ዛሬ ማለዳ ቤቱ ውስጥ አልጋው ላይ እንዳለ ለተገደለው ኤርትራዊ ኋዘን ተዘግተው ውለዋል።
ባለስልጣኖች እንደሚሉት፣ እስካሁን ባለው ጊዜ በተደረገው ምርመራ፣ ነጋዴው የተገደሉት በታጠቁ ዘራፊውች ነው።
የአሜሪካ ድምጽ ባለደረባችን ዲሞ ሲልቫ አውሬልዮ (Dimo Silva Aurelio) ከዋኡ (Wau) የላከውን ዘገባ፣ አዳነች ፍሰሀየ አቀርበዋለች።