ዋሽንግተን ዲሲ —
የደቡብ አፍሪቃው ህገ-መንግሥታዊ ፍርድ ቤት፣ ፕሬዚደንት ጄኮብ ዙማ፣ የግል መኖርያ ቤታቸውን ለማደስ ያለ-አግባብ ተጠቅመውበታል ካለው የመንግሥት ገንዘብ ውስጥ ወደ $16 ሚልዮን የሚሆነውን እንዲመልሱ አዘዘ።
ብይኑ ዛሬ ሓሙስ ይፋ የሆነው፣ ባለሥልጣናት፣ ፕሬዚደንት ዙማን በሌላ በተጠረጠሩበት ወንጀል እየመረመሩ ፍንጭ ባገኙበት ወቅት ነው።
ከጆሃንስበግ ያገኘንውን የቱሶ ኩማሎን ዘገባ አዲሱ አበበ አቅርቦታል፣ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።