በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የመን ከከረመችበት ሁኔታ የምታገግምበት ሰዓት መሆኑን በየመን የ.መ. ድ. አምባሳደር ገለጹ

ፋይል ፎቶ - ህጻን ኡዳይ ፋኢሳል በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክኒያት ባለፈው ወር ሕይወቷን አጥታለች
ፋይል ፎቶ - ህጻን ኡዳይ ፋኢሳል በተመጣጠነ ምግብ እጥረት ምክኒያት ባለፈው ወር ሕይወቷን አጥታለች

በየመን መንግስት፣ በሚደግፈው በሳውዲ የሚመራው ህብረት እና ከሁለት ዓመታት በፊት ዋና ከተማዋን ሰንዓን በተቆጣጠሩት በሁቲዎቹ አማጽያን መካከል ተኩስ አቁሙ የተጀመረው ዕኩለ ሌሊት ላይ መሆኑ የዛሬ ሳምንት ሰኞ ኩዌት ውስጥ ከሚጀመረው የየመን የሰላም ድርድር ታውቋል።

ከአንድ ዓመት በላይ የዘለቀውን ውጊያ ያስቆመውን ውል በደስታ የተቀበሉት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የየመን አምባሳደር ኢስማኤል ኡልድ ሼክ አህመድ አሁን ሃገሪቱ ከከረመችበት ሁኔታ የምታገግምበት ሰዓት ነው ብለዋል።

በየመን መንግስት፣ በሚደግፈው በሳውዲ የሚመራው ህብረት እና ከሁለት ዓመታት በፊት ዋና ከተማዋን ሰንዓን በተቆጣጠሩት በሁቲዎቹ አማጽያን መካከል ተኩስ አቁሙ የተጀመረው ዕኩለ ሌሊት ላይ መሆኑ የዛሬ ሳምንት ሰኞ ኩዌት ውስጥ ከሚጀመረው የየመን የሰላም ድርድር ታውቋል።

ሁሉም ወገኖች ተኩስ አቁሙን እናከብራለን ሲሉ ቃል ገብተዋል። የተ. መ. ድ. የየመን አምባሳደር አያይዘውም ከመጠን በላይ ለተራዘመ ጊዜ በብጥብጥ ስትታመስ የቆየቸውን ሀገር መልሶ ለመገንባት አሁን ዕድል ተፈጥሯል ብለዋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በበኩላቸው ዛሬ ጠዋት በትዊተር ባወጡት የድጋፍ መግለጫ በየመን ተኩስ አቁሙ ስራ ላይ በመዋሉ ደስታ ተስምቶናል ካሉ በሁዋላ ሁሉም ወገኖች ለህዝቡ ሰብዓዊ ርዳታ እንዲገባ እንድፈቅዱ እና ለግጭቱ ፖሌቲካዊ መፍትሄ እንዲገኝ ጥረት እንዲያካሂዱ ተማጽነዋል።

እንደሶሪያው ተኩስ አቁም ሁሉ የየመኑም ተኩስ አቁም ውል ተፈራራሚዎች ሰብዓዊ ርዳታ እንዲገባ ለመፍቀድ ቃል ገብተዋል። ኦክስፋም፣ ህጻናት አድን እና የዴንማርክ የስደተኞች ምክር ቤትን ጨምሮ አስራ አምስት የረድዔት ድርጅቶች ያሉበት ስብስብ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለየመን የሚያስፈልገውን ወጪ በሙሉ እንዲሰፍን አሳስበው።

XS
SM
MD
LG